17 May 2019

የዳኝነት ሚና

የዳኞች ሚና በስነ-

ስርዓት ረገድ በኮመን ሎው እና ሲቪል ሎው አገራት መካከል ያለው የመርማሪ (inquistiorial) እና የሙግታዊ (adversarial) አቀራረብ የአስተዳደር ጉባዔና የመደበኛ ፍ/ቤት የልዩነት ነጥብ ተደርጐ ይወሰዳል፡፡ በሁለቱ የህግ ስርዓቶች ጉባዔዎች በጉዳዩ ወይም በክርክሩ ላይ ካላቸው ቀጥተኛ ተሳትፎ አንጻር አካሄዳቸው የመርማሪነት እንደሆነ ስምምነት አለ፡፡ ከስምምነቱ ባሻገር ብዙዎቹ የመስኩ ባለሙያዎች የአስተዳደር ጉባዔ ይህን መርማሪ አካሄድ መከተል እንዳለበት ጠንካራ መከራከሪያ ያቀርባሉ፡፡
እንደ ፒተር ሌይላንድ እና ቴሪውድስ ገለጻ፤
የአስተዳደር ጉባዔ መርማሪ የስነ-ስርዓት አቀራረብ መከተል ይኖበታል፡፡ ይህ ሲሆን ነው በጉዳዩ ላይ በቀጥታ ምርመራ በማድረግ ፍትህ መሰራቱን ማረጋገጥ የሚችለው፡፡
መርማሪ በሆነው አካሄድ እውነትን ፈልፍሎ ማውጣት ለተከራካሪ ወገኖች ብቻ የሚተው ሳይሆን ችሎቱን የሚመራው ዳኛም በንቃት ይሳተፍበታል፡፡ ይህ መርማሪ የክርክር አመራር ስርዓት በመደበኛው የፍትሐ ብሔር ሙግት ላይም የሚታይ ቢሆንም በገዘፈ መልኩ በተጨባጭ የሚንፀባረቀው ግን በአስተዳደር ጉባዔ በሚካሄዱ ክርክሮች ላይ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment

Popular posts

Recent Posts

LikeBtn

Type

አስተማሪ የሆኑት የችሎት ድራማ ቪዲዮዎች

DOCUMENT & FILES

Criminal Procedure Code 6/2013 PDF by ሕግ እና ፍትህ on Scribd