19 Nov 2020

በመከላከያ ሰራዊት አዋጅ 1100/2019፣ ክፍል 2 አንቀፅ 8 መሰረት፣


 "ማንኛውም ምልምል ወታደር መሰረታዊ የዉትድርና ስልጠናውን እንዳጠናቀቀ [...ህዳግ/omitted...] ወታደራዊ ቃለ-መሐላ ይፈፅማል" ይልና፣ አንቀፅ 9 (2) ደግሞ "ማንኛውም የሰራዊት አባል ፣ ሕገ-መንግስቱን እና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን የማክበርና ማስከበር ግዴታ" እንዳለበት፣ የቃለ-መሃላው ዋና አላማም ሕገ-መንግስቱንና የህገመንግስታዊ ስርዓቱን ማስከበር መሆኑን ይጠቁማል።

 ፪) ትዕዛዝ/Order:


 በተጨማሪ፣ በአዋጁ ክፍል 2፣ አንቀፅ 9፣ ንዑስ አንቀፅ (3) መሰረት፣ "የሰራዊቱ አባል፣ ሌሎች የሃገሪቱን ህጎች፣ ወታደራዊ ህጎች፣ መመሪያዎችና ቛሚ ትእዛዞችን የማክበር ግዴታ[ም]" እንዳለበት ያስረዳል።


 (ለ) የህጎች ተዋረድ /Hierarchy of Laws:


 ፩) ሕገ-መንግስት /Constitution:
 በኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 9 (1): "ሕገ-መንግሥቱ የሀገሪቱ የበላይ ሕግ ነው፡፡ ማንኛውም ሕግ፣ ልማዳዊ አሰራር፣ እንዲሁም የመንግሥት አካል ወይም ባለሥልጣን ውሳኔ ከዚህ ሕገ መንግሥት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈጻሚነት አይኖረውም" በማለት ሕገ- መንግስቱ የሀገሪቱ የበላይ ህግ (supreme law) ብቻ ሳይሆን ማንኛውም የመንግስት ባለስልጣን ትእዛዝ፣ ውሳኔ፣ ደንብ፣ አዋጅ ወዘተ…ከሕገ-መንግስቱ ከተቃረነ ተፈፃሚነት እደሌለው ያስረዳል።


 በሆኑም፣ አንድ የሰራዊት አባል ቃል ከገባለት የህገመንግስት ድንጋጌ የማይቃረኑ ውሳኔዎችን፣ ትእዛዞችን፣ መመሪያወችን ብቻ ያከብራል ማለት ነው። በ ሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 9 (1) በግልፅ እንደሰፈረው፣ የማናቸውም የመንግስት ባለስልጣን፣ የአስፈፃሚ አካል እና ሃላፊ ትእዛዝ ወይም መመሪያ የሕገመንግስቱን መሰረታዊ መርሆዎች ከጣሰ ተፈፃሚ እንደማይሆን ያመላክታል።


 ፪) የበታች ህጎች/ Subordinate Legislations:


 ሕገ-መንግስቱን ለመሙላት የሚወጡት የበታች ህጎች፣ ለምሳሌ፥ የፓርላማ አዋጆች፣ የሚኒስትሮች ምክር-ቤት ደንቦች፣ የመከላከያ ሚኒስቴር መመሪያዎች፣ የበላይ መኮነን ትእዛዞች ከሕገመንግስቱ ተቃርኖ ካላቸው ቅድሚያ ሊሰጠዉ የሚገባው ሕገ-መንግስቱ ይሆናል ማለት ነው።


 (ሐ) ትዕዛዝ ወይስ ቃለ-መሀላ/Order vs. Oath?


 ሕገ-መንግስት የህጎች የበላይ ስለሆነና የሰራዊት አባላት በቀዳሚነት ቃለ-መሃላ የሚገቡት ህገመንግስቱን ለመጠበቅ በመሆኑ፤ በሌላ መልኩ፣ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች እና ትእዛዞች ተፈፃሚነታቸዉ ከሕገ-መንግስቱ በታች ስለሆነ፣ የህግ ተቃርኖ ሲከሰት፣ ከመመሪያ፣ ደንብ ወይም ሌላ ህግ ይልቅ ልእልና ላለው ሕገ-መንግስት እና ለህሊናችው ታማኝ ይሆናሉ ማለት ነው።


 (መ) አለማቀፍ ልምዶች/International Norms:


 አለመረጋጋትና ብጥብጥ በሰፈነባቸው ሃገራት የመከላከያ ሰራዊት ጣልቃ እንዲገባ በሚታዘዝበት ወቅት ሰራዊቱ ሶስት መሠረታዊ የህሊና ግጭቶችን ያስተናግዳል:


 ● እንዲከላከልና እንዲጠብቅ ቃል የገባለት ሲቪል ዜጋ ላይ ጉዳት ማድረስ የሚፈጥረው የስነልቦና ተፅእኖ (insoluble moral dilemma)፣


 

 ●ጉዳት ካደረሰ ሊከተል የሚችለውን በ አለም አቀፍ የጦር ወንጀለኛ ፍርድ ቤት (international military tribunal) ተጠያቂነት ስጋት፤


 ● በሌላ መልኩ፣ የበላይ አለቃን ትእዛዝ (superior order) ባለማክበር የማእረግ መነጠቅ (reduction in rank)፣ ያለ ክብር መሰናበትና (dishonorable discharge) ብሎም በወታደር ፍርድ ቤት (martial court) መጠየቅን እስከ መፍራት ይደርሳል::



 ፩ኛ) ምሽግ መቀመጥ፣ አለመሳተፍ/Quartering:


 በመንግስትና ዜጎች መካከል ፍጥጫ፣ የርስበርስ ግጭት፣ ህዝባዊ አመፆች ሲቀሰቀሱ፣ ያንዳንድ ሃገራት ልምድ እንደሚያሳየው፣ የሰራዊት አባላት ምሽግ ውስጥ ወይም የተለየ ቦታ በመቀመጥ፣ በገለልተኝነት የየትኛውንም ጎራ ባለመደገፍ (neutral/passive)፣ ሊከሰት ይችል የነበረን አላስፈላጊ ደም መፋሰስ በማስቀረት፣ ሰላማዊ፣ ህጋዊና ሁሉን ያሳተፈ ዘላቂ መግባባት እንዲፈጠር የሚያደርጉበት ስልት አንድ ቦታ በመቀመጥ አለመሳተፍ /quartering/ ነው።

የአስተዳደር ጥፋት ምንድነው?

የአስተዳደር ጥፋት ምንድነው?

የእንባ ጠባቂን የስልጣን ገደብ በመወሰን ረገድ ዓብይ ትኩረት ከሚሹ ጉዳዮች መካከል ‘የአስተዳደር ጥፋት’ ለሚለው አገላለጽ የሚሰጠው ፍቺ ትልቁን ቦታ ይይዛል፡፡ እንባ ጠባቂው የሚቀርብለት አቤቱታ የአስተዳደር ጥፋት ተብሎ የሚፈረጅ አይነት ካልሆነ ጉዳዩን ተቀብሎ የመመርመር ስልጣን የለውም፡፡ የአስተዳደር ጥፋትን የማይመለከት አቤቱታ ከእንባ ጠባቂው የስልጣን ክልል ስለሚያልፍ አቤቱታውን ተቀብሎ ከማስተናገድ መቆጠብ ይኖርበታል፡፡

ለዚህ ደግሞ በአስተዳደር ጥፋት ስር የሚጠቃለሉትን ድርጊቶች፣ እርምጃዎችና ውሳኔዎች ምንነት፣ አይነትና ይዘት ግልጽ በሆነ መለኪያ መለየት ይጠይቃል፡፡ የእንባ ጠባቂ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ‘የአስተዳደር ጥፋት’ በእንግሊዘኛው maladministration የሚል አቻ ትርጉም ተሰጥቶታል፡፡ በአዋጁ መግቢያ ደግሞ ይኸው የእንግሊዝኛ ቃል ‘አስተዳደራዊ በደል’ ለሚለው የአማርኛ ቃል ወካይ ትርጉም ሆኖ ተጠቅሷል፡፡
ምንም እንኳን አዋጁ የአስተዳደር በደል የሚለውን አገላለፅ በመግቢው ላይ አንድ ጊዜ ብቻ የተጠቀመበት ቢሆንም በተወሰነ መልኩ የአስተዳደር ጥፋት እና የአስተዳደር በደል ተመሳሳይ ትርጓሜ እንዳላቸው አመላካች ይመስላል፡፡ አዋጁ ሲረቅቅ በጊዜው በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የህግና የአስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት ላይ ‘የአስተዳደር በደል’ የሚለውን ቃል የተጠቀመ ሲሆን ለቃሉ የሚሰጠው ፍቺም የእንባ ጠባቂውን ስልጣን በመወሰን ረገድ ዋናውና ቁልፍ ስለመሆኑ አስምሮበታል፡፡ ቁልፍና ወሳኝ ጉዳይ ቢሆንም የአስተዳደር ጥፋቶች የሚባሉት የትኞቹ ናቸው? ለሚለው ጥያቄ ማቋቋሚያ አዋጁ ግልጽና የማያወላዳ መለኪያ ሳያስቀምጥ አልፎታል፡፡ በአዋጁ የትርጓሜ ክፍል ላይ ‘የአስተዳደር ጥፋት’ ምንነት እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡
የአስተዳደር ጥፋት ማለት ማናቸውንም የአስተዳደር ህግን፣ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ህግን ወይም አስተዳደር ነክ ህጐችን በመጻረር በመንግስት አስፈፃሚ አካላት የሚፈፀሙ ድርጊቶችን ወይም የሚሰጡ ውሳኔዎችን ይጨምራል፡፡a
የድንጋጌውን ግልጽነት በሚገባ ለመፈተን የሚከተሉትን ምሳሌዎች እንመልከት፡፡ በመንግስት ዩኒቨርሲቲ በሚማሩ ተማሪዎች በሚከተሉት ሁኔታዎች የአስተዳደር በደል ተፈፅሞብኛል የሚል አቤቱታ ለእንባ ጠባቂው ሊቀርብ ይችላል፡፡
  • በአንድ የትምህርት አይነት የወሰድኩት ፈተና ትክክለኛ መልሱን የመለስኩ ቢሆንም አለአግባብ ዝቅተኛ ውጤት ተሰጠኝ፡፡
  • የዩኒቨርሲቲው ሬጅሰትራር አማካይ ውጤቴን ከሴኔት ደንብ ውጭ በማስላት ዝቅ አድርጐብኛል፡፡
  • ወደ ዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ የመግቢያ ሰዓት እስከ ምሽቱ 3፡00 ሰዓት ብቻ እንዲሆን መደረጉ የመንቀሳቀስ መብታችንን የሚጋፋ ነው፡፡
  • ጥፋት ሳልፈጽምና ስለመፈጸሜም በቂ ማስረጃ ሳይኖር አለአግባብ ከዩኒቨርሲቲው በዲሲፒሊን ተባረርኩኝ፡፡
  • የወጪ መጋራት ክፍያ ካልከፈልክ የትምህርት ማስረጃ አይሰጥህም ተባልኩኝ፡፡
  • ከምሽቱ አራት ሰዓት በኋላ በግቢው ውስጥ ከወንድ ጋር ተገኝተሻል በሚል ዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ዲሲፒሊን መተዳደሪያ ደንብ ጠቅሶ እንድቀጣ ተደርጌያለሁ፡፡ ስለሆነም ህገ- መንግስቱን በተጻረረ መልኩ በወጣ ደንብ የተወሰደብኝ ቅጣት እንዲነሳልኝ፡፡
  • በተወሰደብኝ የዲሲፕሊን እርምጃ ላይ ለዩኒቨርሲቲው የበላይ አካል ያቀረብኩት ይግባኝ አለአግባብ ምላሽ ሳይሰጠው ዘግይቷል፡፡
  • የመኝታ ክፍላችን (ዶርም) ከህግና ከህገ መንግስት ውጭ በጥናት ደክመን በምንተኛበት ወቅት እኩለ ለሊት ላይ በግቢው የጥበቃ አባላት ይፈተሻል፡፡
  • የተመደበልን መምህር እንዲቀየርልን በተደጋጋሚ ለዩኒቨርሲቲው ያቀረብነው ጥያቄ ተገቢ ምላሽ አልተሰጠውም፡፡
  • የሚቀርብልን ምግብ ጥራቱን የጠበቀ አይደለም፡፡
  • ወደ ዩኒቨርሲቲው መግቢያ የሚወስደው መንገድ መብራት ስለሌለው በሴት እህቶቻችን ላይ ጥቃት እየደረሰ ነው፡፡ ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እና ለኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ላቀረብነው ተደጋጋሚ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ አልተሰጠንም፡፡
ከላይ ከቀረቡት መላምታዊ ምሳሌዎች መገንዘብ እንደሚቻለው በአንድ የመንግስት ተቋም ውስጥ ብቻ የተራራቀ ይዘት ያላቸው የተለያዩ የቅሬታ ምክንያቶችን መሰረት ያደረጉ አቤቱታዎች ለእንባ ጠባቂው ይቀርባሉ፡፡ ተቋሙ አንድን አቤቱታ ተቀብሎ ከማስተናገዱ በፊት አቤቱታው እውነት ነው ተብሎ ቢገመት የአስተዳደር ጥፋት ተብሎ ሊፈረጅ የሚችል ስለመሆኑ በቅድሚያ ማረጋገጥና መወሰን ይኖርበታል፡፡
ማናቸውም አቤቱታ ተመርምሮ ለአቤቱታ አቅራቢው መፍትሔ ሊሰጥ የሚችለው ይህ ጥያቄ መጀመሪያ ከተመለሰ በኋላ ነው፡፡ የቀረበው አቤቱታ የአስተዳደር ጥፋትን የማይመለከት ከሆነ ምርምራ ሳይጀመር ውድቅ መደረግ ይኖርበታል፡፡ በህጉ ላይ ለአስተዳደር ጥፋት የተሰጠው ትርጓሜ የእንባ ጠባቂውን ፈተና አያቃልልም፡፡ በደፈናው ሲታይ በአዋጁ ላይ ለአስተዳደር ጥፋት የተሰጠው ትርጓሜ ከህግ ውጪ የተፈጸመ ድርጊትን ብቻ የሚሸፍን ይመስላል፡፡ በዚህ መልኩ ከተረዳነው የአስተዳደር ጥፋት ይዘት የእንባ ጠባቂውን ስልጣን በጣም ያጠበዋል፡፡
የአስተዳደር ጥፋት በግልፅ የተቀመጠን ህግ መጻረር ብቻ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ‘የመንገድ መብራት ባለመኖሩ ምክንያት ለጾታዊ ጥቃት ተጋለጥን፣ ለጥያቄያችንም በቂ ምላሽ አልተሰጠንም፡፡’ የሚል አቤቱታ ‘ህግ መጻረር’ ውስጥ አይካተትም፡፡ ሆኖም ለዜጐች ተገቢ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ በአፋጣኝ አለመስጠት የአስተዳደር ጥፋት ስለመሆኑ አያከራክርም፡፡
በተመሳሳይ መልኩ አንዳንድ ጉዳዮች የአስተዳደሩ የውስጥ ጉዳዮች በመሆናቸው ለአስተዳደሩ ለራሱ መተው ያላባቸው ናቸው፡፡ ህገ መንግስታዊው የስልጣን ክፍፍል መርህ እንባ ጠባቂው ራሱን በአስተዳደሩ ምትክ ቦታ እንዳያስገባ ገደብ ያደርግበታል፡፡

የምርመራ አካሄድ ስርዓትና መፍትሔዎች

እንባ ጠባቂ ተቋም እና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የቀረበላቸው አቤቱታ ይዘት በስልጣናቸው ክልል ውስጥ የሚወድቅ ከሆነ ቀጣዩ ተግባር የአስተዳደር ጥፋት ወይም የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈፀሙንና ጥፋቱ የተፈፀመበትን ሁኔታ ብሎም የጥፋቱን ደረጃ ለመወሰን ምርመራ ማከናወን ነው፡፡ ምርመራው አቤቱታ ባይቀርብም በራስ ተነሳሽነት ሊካሄድ ይችላል፡፡ ቅሬታ በደረሰበት ወገን የሚቀርበው አቤቱታ የግድ በማስረጃ የተደገፈ መሆን አይኖርበትም፡፡ ከአቤቱታ አቅራቢው የሚጠበቀው ‘በተቻለ መጠን’ ደጋራ ማስረጃ ማቅረብ ነው፡፡
በዚህ የምርመራ ሂደት ውስጥ ተመርማሪው አካል መልሱን የማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ በማያሻማ መልኩ አልተገለጸም፡፡ በሁለቱም አዋጆች አንቀጽ 25 መሰረት ተመርማሪዎች መልስ እንዲሰጡ ማድረግ የመርማሪው ስልጣን እንጂ የተመርማሪው መብት አይደለም፡፡
የምርመራው አካሄድና ስርዓት በተመለከተ ሁለቱም ተቋማት በማቋቋሚያ አዋጃቸው አንቀጽ 24 የተሰጣቸው ስልጣን ተግባራቸውን በሚገባ ለማከናወን በሚገባ፡፡ በአንቀጽ 24 መሰረት የምርመራ ስልጣን፤
  1. ተመርማሪዎች ለጥያቄ እንዲቀርቡ ወይም መልስ እንዲሰጡ
  2. ምስክሮች ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ
  3. በሶስተኛ ወገን እጅ ያለ ማስረጃ እንዲቀርብ ማድረግን ይጨምራል፡፡
በምርመራ ሂደት ውስጥ ሆነ በሌሎች የተቋሙና የኮሚሽኑ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ማንኛውም ሰው በተለይም አስፈፃሚ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ የመስጠትና የመተባበር ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ በተወሰኑ ሁኔታዎች ለመተባበር ፍቃደኛ አለመሆን የወንጀል ተጠያቂነት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ተቋሙ እና ኮሚሽኑ ምርመራቸውን ሲያከናውኑ መጥሪያ ተቀብሎ ካለበቂ ምክንያት መቅረት፣ ሰነዶች ለመስጠት ወይም ለማስመርመር ፍቃደኛ አለመሆን እንዲሁም ቀርቦ መልስ ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆን ከአንድ ወር እስከ 6 ወር በሚደርስ እስራት ወይም ከብር ሁለት መቶ እስከ አንድ ሺህ በሚደርስ ገንዘብ መቀጫ ወይም በሁለቱም ያስቀጣል፡፡
 

የኢትዮጵያ የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም

የኢትዮጵያ የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም

አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት (ከፊል የህግ አውጭነት ስልጣን)


አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት (ከፊል የህግ አውጭነት ስልጣን)
ህግ የማውጣት ስልጣን የህግ አውጭው ነው እንላለን እንጂ በተግባር ግን ህግ የሚወጣው በተወካዮች ም/ቤት ብቻ አይደለም፡፡ ይህ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በየትም አገር ያለ እውነታ ነው፡፡ በየጊዜው እያደገ ከሚመጣው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ውስብስብነት የተነሳ ህግ አውጭው ከልሂቅ እስከ ደቂቃ ለእያንዳንዱ ችግር መፍትሄ የሚሆን ህግ በአይነትና በጥራት ማቅረብ ይሳነዋል፡፡ አንድ የህግ ረቂቅ ውጤት ያለው ህግ ለመሆን ከሚፈጀው ረጅም ጊዜና ዝርዝር የስነ-ስርዓት ቅድመ ሁኔታ አንፃር ህግ አውጭው በየጊዜው ለሚፈጠር ችግር በየጊዜው አዋጅ እያወጣ መፍትሄ ለመስጠት በቂ ጊዜ የለውም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አንዳንድ ዝርዝር ጉዳዮች ልዩ እውቀትን የሚጠይቁ እንደመሆኑ ውስን የሆነው የህግ አውጭው እውቀት የህግ ማውጣት ስልጣን በተግባር በከፊል የተገደበ እንዲሆንና ሌላ አማራጭ እንዲፈልግ ያስገድደዋል፡፡
ይህ አማራጭ በውክልና ስልጣን የሚወጣ ህግ (delegated legislation) ይባላል፡፡ ተግባራዊ ከሆኑት አስፈላጊ ምክንያቶች የተነሳ ህግ አውጭው ከህዝብ የተሰጠውን ህግ የማውጣት ስልጣን በከፊል ቆርሶ ለስራ አስፈፃሚውና ለአስተዳደር መ/ቤቶች ይሰጣል፡፡ በዚሁ መሰረት የሚኒስትሮች ም/ቤት በአዋጅ በሚሰጠው ስልጣን መሰረት ደንብ ይደነግጋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የአስተዳደር መ/ቤቶች በውክልና የህግ አውጭነት ስልጣናቸው መመሪያቸውን ያወጣሉ፡፡
ዋነኛ ስልጣኑ ህግ ማስፈፀም የሆነው ስራ አስፈፃሚው የመንግስት አካል በደንብና በመመሪያ የህግ አውጭነት ስልጣን ደርቦ መያዙ ከስልጣን ክፍፍል መርህ ጋር የሚጣረስ ቢሆንም የህግ አውጭው ጊዜና የእውቀት ውስንነት እንዲሁም የመንግስት አስተዳደርን ብቁና ውጤታማ ከማድረግ አንፃር በተግባር የግድ የሚል እውነታ ሆኗል፡፡ ሆኖም አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት ስልጣን በዚህ እውነታ ብቻ አይቋጭም፡፡
ያልተገደበ ስልጣን መኖር ለዜጐች መብትና ነፃነት መቼም ቢሆን አደገኛነቱ ጥርጥር የለውም፡፡ የአስፈላጊነቱ እውነታ ከዜጐች መብትና ነፃነት ጋር እንዲጣጣም ወይም እንዲታረቅ ተግባራዊ የስልጣን መቆጣጠሪያ መሳሪያ እንዲኖር ግድ ይላል፡፡ እንደ የአስተዳደር ህግ ምሁሩ ዌድ አገላለጽ ‘ከዜጐቹ ላይ ነፃነት ሲቀነስ ፍትህ መጨመር አለበት፡፡’ የመንግስት ስልጣኑ ሲለጠጥ በዛው ልክ የዜጐች መብትና ነፃነት እየተሸበሸበ (እያነሰ) ይመጣል፡፡ ስልጣን ሲጨምር ፍትህም አብሮ መጨመር አለበት፡፡ ከዚህ አንጻረ ስራ አስፈፃሚው ተጨማሪ የህግ አውጭነት ስልጣን ሲሰጠው ስልጣኑን በአግባቡና ፍትሀዊ በሆነ መንገድ እንደሚገለገል የሚያረጋግጥና የሚቆጣጠር የአስተዳደራዊ ድንጋጌ አወጣጥ ስነ ስርዓት ያስፈልጋል፡፡
በሚኒስትሮች ም/ቤት እና በአስተዳደር መ/ቤቶች የሚወጡ አስተዳደራዊ ድንጋጌዎች ከሌሎች የአስተዳደር ተግባራት የሚለያቸው መሰረታዊ ባህሪያት አላቸው፡፡ በዋናነት የሚከተሉትን ነጥቦች ይጠቀሳሉ፡፡
  • በውክልና የሚወጣ ህግ የተፈጻሚነቱ ወሰን በአንድ ግለሰብ ወይም ድርጅት ላይ ሳይሆን በህብረተሰቡ በአጠቃላይ ወይም በተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል ላይ ነው፡፡
  • ትኩረቱ በግለሰብና በመንግስት መካከል የሚነሱ የግል ክርክሮችን መፍታት ሳይሆን የህዝብ ጥቅምን ለማስጠበቅ የሚረዱ ፖሊሲዎችን ማስፈፀም ነው፡፡
  • ወደ ኋላ ተመልሶ ተመልሶ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡ ውጤቱና ተፈጻሚነቱ አስተዳደራዊ ድንጋጌው ከወጣ በኋላ ወደ ፊት ለሚከሰቱ ነገሮች ነው፡፡
  • አብዛኛውን ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ ውጤት ይኖረዋል፡፡
  • በይፋ ታትሞ ለህዝብ መሰራጨት ይኖርበታል፡፡
  • ከህትመት በፊት ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት የማማከር ቅድመ ሁኔታ ሊሟላ ይገባል፡፡
  • በአስተዳደሩ የሚወጡ ድንጋጌዎች አብዛኛውን ጊዜ በተግባር እንዲፈፀሙ በተጨማሪ የአስተዳደር ድርጊት /ውሳኔ፣ እርምጃ፣ ቅጣት/ መታገዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ስለዚህም በራሳቸው ምሉዕ አይደሉም፡፡

Popular posts

Recent Posts

LikeBtn

Type

አስተማሪ የሆኑት የችሎት ድራማ ቪዲዮዎች

DOCUMENT & FILES

Criminal Procedure Code 6/2013 PDF by ሕግ እና ፍትህ on Scribd