This blog is for individuals and private organizations who want to read the FDRE Constitution as well as the interpretations of the Constitution as well as various laws of our country, various proclamations, government-approved directives, teachings and publications. Laws and the Constitution of our country. It is a website where we volunteer to help the public learn about draft laws and interpretations of the constitution.
13 May 2021
ET-law: Seera Yakkaa Mootummaa,--Kitaaba Afuraffaa
2 May 2021
በኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ አንቀጽ 23/1/ መሰረት ድርጊት ማለት በሕግ የተከለከለውን ማድረግ ወይም በህግ የታዘዘውን አለማድረግ ማለት እንደሆነ ተቀምጧል፡፡
![]() |
አንድን ድርጊት መፈፀም ወይም አለመፈፀም ወንጀል የሚሆነው በመንግስት /በዐቃቤ ሕግ/ የሚያስከስስና በህግ የሚያስቀጣ ሲሆን ነዉ፡፡ ወንጀል የሚባለው አንድ ሰው ለህገወጥ ድርጊቱ በመንግስት የሚቀጣ ሆኖ በግልፅ ህግን የመጣስ ድርጊት ሲፈፅም ነው የሚያስቀጣ ወንጀል ማለት ሕገወጥነቱና አስቀጪነቱ በሕግ የተደነገገውን ድርጊት መፈፀም ማለት ነው፡፡
በኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ አንቀጽ 23/1/ መሰረት ድርጊት ማለት በሕግ የተከለከለውን ማድረግ ወይም በህግ የታዘዘውን አለማድረግ ማለት እንደሆነ ተቀምጧል፡፡
ለምሳሌ በሐሰተኛ ሰነድ መገልገል የሚያስቀጣ ወንጀል መሆኑ በኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ አንቀጽ 378 በግልፅ ተደንግጓል፡፡ ማንም ሰው በሐሰት በተዘጋጀ ወይም ወደሐሰት በተለወጠ ሰነድ እያወቀ የተገለገለበት እንደሆነ በሦስት ወር በማያንስ ቀላል እስራት፣ ወይም ነገሩ በጣም ከባድ በሆነበት ጊዜ ከአሥር አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ መረዳት ይቻላል፡፡ ስለዚህ ይህንን ድንጋጌ ተላልፎ መገኘት ለተቀመጠው የወንጃል ቅጣት የሚዳርግ ይሆናል፡፡
አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለው ወንጀሉን የሚያቋቁሙት ሕጋዊ፣ ግዙፋዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ እንደሆነ የወንጀል ህጉ በግልፅ የስቀምጣል፡፡
አንድ ወንጀል ማስቀጣት የሚችለው ፍርድ ቤት ወንጀሉን መፈፀሙን ሲያረጋግጥና ቅጣት የሚጣልበት ሆኖ ሲያገኘው ነው፡፡ ወንጀል ፈፃሚው ወንጀል መፈፀሙ በፖሊስ ተመርምሮ፣ በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶ በፍረድ ቤት ከተወሰነበት በኋላ ተፈጻሚ ሊሆኑ ሚችሉ ቅጣቶች ይተላለፋሉ፡፡ ቅጣቶቹም የግዴታ ስራ፣ የገንዘብ መቀጮ፣ እስራት (ቀላልና ከባድ) ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
በኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ የተመለከቱት ቅጣቶችና የጥንቃቄ እርምጃዎች ህጉ ሊደርስበት ያሰበውን ዓላማ ለማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ በህጉ መንፈስ መሰረት መፋፀም አለባቸው፡፡ የወንጀል ሕግ አላማ፣ ለጠቅላላ ጥቅም ሲባል የአገሪቱን መንግስት፣ የህዝቦቹን፣ የነዋሪዎቹን ሰላም፣ ደህንነት፣ ሥርዓት፣ መብትና ጥቅም መጠበቅና ማረጋገጥ ነው፡፡
ቅጣቶቹና የጥንቃቄ እርምጃዎቹ ምንጊዜም ሰብአዊ ክብርን በሚጠብቅ መንገድ መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡ በኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ አንቀጽ 87 ተቀምጧል፡፡ በሀገራችን ኢሰባዊ አያያዝ በጠብቅ የተከለከለ መሆኑ በኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት አንቀጽ 18 ስር በግልፅ ተደንግጓል፡፡
ይርጋ ማለት ምን ማለት ነዉ?
ይርጋ ማለት አንድን ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት ይዞ ለመምጣት የተፈቀደ ጊዜ ማለት ነው፡፡ ሁሉም ጉዳዮች በማንኛውም ጊዜ በዘፈቀደ በማንኛውም ሰዓት ወደ ፍርድ ቤት የሚመጣ ከሆነ የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ የሚቃውስ ከመሆኑም በላይ ሰዎች የተረጋጋ ህይወት እንዳይኖሩ ስለሚያደርጋቸው አብዛኛው የህግ ድንጋጌዎችን ማስፈፀምያ ጊዜ ገደቦች እንዳሉ እንገነዘባለን፡፡
በኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ የተለያዩ የይርጋ ድንጋጌዎች ያሉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የተወሰኑትን ማለትም የክስ፣ የቅጣት፣ የጥንቃቄ አርምጃዎች ና ሌሎች የይርጋ ዘመንን በቅደም ተከተላቸው በመመልከት በመጨረሻ የቅጣት አይነቶችን ባጭሩ እንመለከታለን፡፡
2. የክስ ይርጋ
በኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ አንቀጽ 216 ስር በተደነገገው ድንጋጌ መሰረት የይርጋ ዘመን ለተቀመጠላቸው ጉዳዮች በህግ ከተቀመጠላቸው ጊዜ ውጪ ፍርድ ቤቶች የቀረበላቸውን ክስ በዳንኝነት ማየት እንደማይችሉ ተቀምጧል፡፡ ይህም
”በህግ በሌላ አኳኋን ካልተደነገገ በስተቀር ከዚህ በታች የተመለከተው የይርጋ ዘመን ካለፈ በኋላ በማናቸውም ወንጀል የግል አቤቶታን ወይም የወንጀል ክስን መቀበልና ጉዳዩን በዳኝነት ማየት አይቻልም፡፡ የይርጋ ዘመኑ ማለፍ ለማናቸውም የወንጀል ተካፋይ ቅጣትን ያስቀራል፡፡ ለይርጋ የተወሰነ ግዜ ካለፈ የጥፋተኝነት ውሳኔ ወይም ቅጣት ወይም የጥንቃቄ እርምጃ ሊወስን አይችልም፡፡” በማለት አንቀጽ 216 ስር ተቀመጧል፡፡
በወንጀል ህጉ የተቀመጠው ወንጀል የይርጋ ጊዜው ካለፈ በኋላ
የግል አቤቶታን መቀበልና ጉዳዩን በዳኝነት ማየት አይቻልም፡፡
የወንጀል ክስን መቀበልና ጉዳዩን በዳኝነት ማየት አይቻልም፡፡
ለማናቸውም የወንጀል ተካፋይ ቅጣትን የሚያስቀር በመሆኑ የይርጋ ጊዜው ካለፈ በኋላ
የጥፋተኝነት ውሳኔ ወይም
ቅጣት ወይም
የጥንቃቄ እርምጃ ሊወስን እንደማይችል ከተቀመጠው ድንጋጌ መረዳት ይቻላል፡፡
የወንጀል ክሱ በይርጋ ከታገደና ክሱን ለመቀበል የማይገባ ስለመሆኑ ተከሳሹ ባያመለክትም ዐቃቤ ሕጉ ወይም ፍርድ ቤቱ በማናቸውም ጊዜ ማንሳት እንዳለባቸው በኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ አንቀጽ 216 ንዑስ አንቀፅ 2 ስራ ተደንግጓል፡፡ በተጨማሪም በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ህግ አንቀጽ 130 ስር ከተቀመጡት የመጀመርያ መቃወምያዎች መካከል አንደኛው ይርጋ ዘመን ማለፍ እንደሆነ መመልከት እንችላለን፡፡
ሆኖም የይርጋ ዘመን የሌላቸው የወንጀል አይነቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ከዚሁ አንቀጽ መግብያ ላይ ”በህግ በሌላ አኳኋን ካልተደነገገ በስተቀር …” ከሚለው መረዳት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 24 የሽብርተኝነት ወንጀል በይርጋ የማይታገድ መሆኑን በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ ስለዚህ በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ የተመለከተ ማናቸውም የሽብርተኝነት ወንጀል በፈፀመ ሰው ላይ የሚቀርብ ክስ በይርጋ ስለማይታገድ በማናቸውም ጊዜ ሊቀርብ ይችላል፡፡
መደበኛ የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን
የወንጀል ህጉ መደበኛ የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመንን በሚያስቀጡት የቅጣት አይነት ላይ በመመስረት በስድስት ቦታ ከፋፍሏቸው ያስቀመጣቸው ሲሆን እነዚህም በሞት ፍርድ ወይም ዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት፣ ከአስር ዓመት በላይ እስከ ሃያ አምስት ዓመት፣ ከአምስት ዓመት በላይ እስከ አስር ዓመት፣ ከአምስት አመት ለማይበልጥ ፅኑ እስራት፣ ከአንድ ዓመት በላይ በቀላል እስራት፣ እስከ አንድ ዓመት በቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ለሚያስቀጡ ወንጀሎች በማለት ከ25 እስከ 3 አመት ክስ የማቅረብያ የይርጋ ዘመን ተቀምጦላቸዋል፡፡
የወንጀል ህጉ አንቀጽ 217 ንዑስ አንቀፅ 1 “መደበኛ የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን በወንጀል ተግባር ክስ የማቅረብ የይርጋ ዘመን የሚፀናው ከዚህ በታች በተመለከተው መሰረት ነው፡-
ሀ/ የሞት ፍርድ ወይም የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል ሃያ አምስት ዓመት፣
ለ/ ከአስር ዓመት በላይ እስከ ሃያ አምስት ዓመት ለመድረስ የሚችሉ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ሃያ አመት፣
ሐ/ ከአምስት ዓመት በላይ እስከ አስር ዓመት ለመድረስ የሚችል ጽኑ እስራት ለሚያስቀጣ አስራ አምስት አመት፣
መ/ ከአምስት አመት ለማይበልጥ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል አስር ዓመት፣
ሠ/ ከአንድ ዓመት በላይ በቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል አምስት ዓመት፣
ረ/ እስከ አንድ ዓመት በቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወይም በመቀጮ ብቻ ለሚያስቀጣ ወንጀል ሦስት ዓመት፡፡”
በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀፅ 2 ስር ተደራራቢ ወንጀሎች ተፈጽመው ሲገኙ፡- የወንጀሎቹ ከፍተኛ ቅጣቶች ተመሳሳይ በሚሆኑበት ጊዜ የአንዱ ወንጀል የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን በሁለቱም ወንጀሎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆንና የወንጀሎቹ ከፍተኛ ቅጣቶች የተለያዩ ተመሳሳይ በሚሆንበት ጊዜ ከሁሉም ከባድ የሆነው ወንጀል የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን በሌሎች ወንጀሎች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን በግልፅ ያስቀምጣል፡፡
ስለዚህ በመደበኛ የክስ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን ጊዜ ቢያንስ 3 ዓመት ቢበዛ እንደ ጉዳዩ ሁኔታ 25 ዓመት እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡
ልዩ የግል አቤቶታ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን
የወንጀል ህጉ አንቀጽ 218 ልዩ የግል አቤቶታ ማቅረብያ የይርጋ ዘመን ሁለት ዓመት እንደሆነ ደንግጓል፡፡ ማንኛዉም የግል አቤቶታ ጉዳዩ ከተፈፀመ ጊዜ ጀምሮ በሁለት ዓመት ውስጥ ካልቀረበ ጉዳዩ ፍርድ ቤት የማይቀርብና ቀርቦም ከሆነ የቀረበውን ጉዳይ ፍረድ ቤት በዳኝነት ማየት አይችልም፡፡
በአንቀጽ 213 ድንጋጌ መሰረት የግል ተበዳይ ሆኖ የግል አቤቶታ ማቅረብ የሚችል ማንኛውም ግለሰብ ጉዳዩ ከተፈፀመ ጊዜ ጀምሮ በሶስት ወር ውስጥ ካላቀረበ ጉዳዩ ተመርምሮ ወደ ፍርድ ቤት መቅረብ እንዳልፈለገ ተቆጥሮ ወይም የህግ ግምት ተወስዶ አቤቶታው ቀሪ ይሆናል፡፡ ይህ ሶስት ወር በተለያዩ ምክንያት የመቁጠርያው ጊዜ በበቂ ምክንያት ያጋጠሙት ችግር ከተወገደበት ጊዜ መቁጠር የሚጀመርበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ ለምሳሌ የግል ተበዳይ ለአቅመ አዳም ያልደረሰ ከሆነ፣ ለአቅመ አዳም ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ሶስት ዓመቱ የሚቆጠር ይሆናል፡፡
የይርጋ ዘመን አቆጣጠር
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 219 ንዑስ አንቀፅ 1 የይርጋ ዘመን የሚታሰበው የቅጣት ማክበጃ ወይም ማቅለያ ሁኔታዎች ግምት ውስጥ ሳይገቡ በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት መሠረት በማድረግ እንደሆነ ተቀምጧል፡፡ የተፈፀመው ወንጀል በተለዋጭ ወይም በተደራራቢ ተፈፃሚነት ቢኖራቸውም ቅጣቶች የሚያስቀጡ ሲሆኑ የይርጋ ዘመኑ የሚታሰበው ከሁሉም ከባድ ለሆነው ወንጀል በወንጀል ሕግ ልዩ ክፍል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት መሰረት በማድረግ ነው፡፡
በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 እንደተቀመጠው የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው ጥፋተኛው የወንጀሉን ድርጊት ከፈጸመበት ቀን አንስቶ ነው፡፡ የወንጀሉ ድርጊት እየተደጋገመ ተፈፅሞ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የመጨረሻው የወንጀል ድርጊት ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ ነው፡፡ እንዲሁም የወንጀሉ ድርጊት ለረጅም ጊዜ ሲፈፀም የቆየ እንሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የወንጀሉ ድርጊት ካቆመበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ ወንጀሉ ተደርጓል ለማለት የሚቻለው ከፀባዮቹ አንዱ የወንጀሉ ውጤት የሆነ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የወንጀሉ ውጤት ከተገኘበት ግዜ ጀምሮ ነው፡፡
የይርጋ ዘመን መታገድ
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 220 ንዑስ አንቀጽ 1 በሕጉ ወይም በፍሬ ነገር ክሱ እንዳይጀምር ወይም እንዳይቀጥል የሚያግድ መሰናክል እስካለ ድረስ የይርጋ ዘመን መቆጠሩ ታግዶ ይቆያል፡፡ እንዲሁም ክስ ቀርቦ ነገሩ በዳኝነት በመታየት ላይ እንደሆነ ወይም በሌላው ችሎት የቀረበው ክስ ሳይፈፀም ተከሳሹ በተከሰሰበት የወንጀል ክስ ላይ ውሳኔ ሊሰጥ የማይገባ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ ወቆጠር ታግዶ ይቆያል፡፡ መስናከሉም እንደተወገደ ወዲያውኑ
የይርጋ ዘመኑ መቆጠር ይቀጥላል፡፡
በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 ስለክሱ መከታተል አቤቶታ እንዲቀርብ ማስፈለጉ በሕግ ተመልክቶ በተገኘ ጊዜ አቤቶታ አለማቅረብ የይርጋውን መቆጠር አያግድም፡፡ እንዲሁም ክሱ እንዳይጀምር ወይም እንዳይቀጥል ጥፋተኛው በራሱ ፍላጎት የሚፈፀመው ተግባር የይርጋ ጊዜውን መቆጠር አያግደውም፡፡
የይርጋ ዘመን መቋረጥ
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 221 የይርጋ ዘመን መቋረጥ ከወንጀሉ ወይም ከወንጀለኞቹ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ምርመራ እንዲካሄድ ብርበራ እንዲደረግ መጥሪያ እንዲሰጥ ወይም ክስ እንዲቀርብ የሚሰጥ ትዕዛዝ፣ የሚፈፀም ድርጊት ወይም የሚሰጥ ውሳኔ የይርጋ ዘመኑን መቆጠር ያቋርጣል፡፡ የይርጋ ዘመን በተቋረጠ ቁጥር እንደገና እንደ አዲስ መቆጠር ይጀምራል፡፡ የይርጋ ዘመኑ መቋረጥ ፍፁም የሆነ ውጤት አለው፡፡ በወንጀሉ ተካፋይ መሆናቸው ለታወቀውም ሆነ ላልታወቀው ሁሉ መቋረጡ ይፀናባቸዋል፡፡ ይህ ማለት የወንጀል ተካፋይ መሆኑ ወንጀሉ በተከሰተበት ጊዜ ያልተወቁ ሰዎች ያኔ ባለመታወቃቸው ምክንያት የይረጋ መቋረጥ አሰመልክቶ ሊኖረው የሚችል ልዩነት እንደሌለ መረዳት ይቻላል፡፡
ፍፁም የሆነ የይርጋ ዘመን
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 222 ፍፁም የሆነ የይርጋ ዘመን፣ በማናቸውም ምክንያት መደበኛ የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን /አንቀጽ 217/ አጠፌታ ጊዜ (እጥፍ) ካለፈ ወይም ልዩ የግል አቤቶታ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን ሲሆን /አንቀጽ 218/ ከዚሁ ዘመን በግማሽ የሚበልጥ ጊዜ (3 ዓመት) አልፎ እንደሆነ በወንጀሉ ላይ የሚቀርበው ክስ ወይም የሚደረገው መከታተል በይርጋ ቀሪ ይሆናል፡፡
3. የቅጣትና ጥንቃቄ አርምጃዎች ይርጋ
በኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ አንቀጽ 223 ንዑስ አንቀጽ 1 በሕግ በሌላ አኳኋን በግልጽ ካልተደነገገ በስተቀር በተቀጪው ላይ የተወሰነው ቅጣት በማናቸውም ምክንያት ከአንቀጽ 224-228 በተመለከቱት ጊዜያት ውስጥ ሳይፈጸም የቆየ እንደሆነ ቅጣቱን የማስፈፀም መብት ቀሪ ይሆናል፤ የተወሰነውም ቅጣት ወይም የጥንቃቄ እርምጃ ሊፈፀም አይችልም፡፡ የዋነኛው ቅጣት የይርጋ ዘመን የተጨማሪ ቅጣቶችና የጥንቃቄ እርምጃዎች መፈፀምንም ያስቀራል፡፡ እንዲሁም የዋናው ቅጣት የይርጋ ዘመን ከቅጣት ጋር ለተያያዘ የንብረት መውረስ ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡ ሆኖም የጥንቃቄ እርምጃዎች ያለዋነኛ ቅጣት (ማለትም ራሳቸውን ችለው ለብቻቸው) በሚወሰኑበት ጊዜ የአንቀጸ 224/1/መ ድንጌዎች ተፈፃሚ ስለሚሆን በ 5 ዓመት ቀሪ ይሆናል፡፡
በዚሁ ዐንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 ጉዳዩ የሚመለከታቸው የዳኝነት ወይም የአስተዳደር ባለስልጣኖች በራሳቸው ተነሳሽነት የቅጣት የይርጋ ደንብን አክብሮ የመጠየቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ይህ ማለት የይርጋው ጊዜ ሳይጠናቀቅ አስቀድሞ ቅጣቱን ወይም የጥንቃቄ እርምጃውን ማስፈፀም እንደሚኖርባቸው ያመለክታል፡፡
በተጨማሪም በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 ስር የተወሰነው ቅጣት በይርጋ ዘመኑ መታገድ ምክንያት ሳይፈፀም ቢቀርም በወንጀለኞች መዝገብ ውስጥ እንደተመዘገበ እንደሚቆጠር ያስቀምታል፡፡
መደበኛ የቅጣት ይርጋ ዘመን
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 224 ንዑስ አንቀጽ 1 የቅጣትና የጥንቃቄ እርምጃዎች ይርጋ ዘመን የሚፀናው ሁኔታን አስቀምጧል፡፡
ሀ/ ለሞት ፍርድ ወይም ለዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ሠላሳ ዓመት፣
ለ/ ከአስር ዓመት በላይ ለሆነ ነፃነትን የማሳጣት ቅጣት ሃያ ዓመት፣
ሐ/ ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ ነፃነትን የማሳጣት ቅጣት አሥር ዓመት፣
መ/ ለማናቸውም ሌላ ቅጣት ወይም የጥንቃቄ እርምጃ ውሳኔ አምስት ዓመት
በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 ተደራራቢ ቅጣቶች ተወስነው እንደሆነ ቀላል የሆኑት ቅጣቶች በይርጋ ቀሪ የሚሆኑት ከሁሉም ከባድ የሆነው ቅጣት በይርጋ ቀሪ የሚሆንበት ጊዜ እንደሆነ ተደንግጓል፡፡
የቅጣት ይርጋ ዘመን አቆጣጠር
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 225 ንዑስ አንቀፅ 1 የቅጣት ይርጋ ዘመን መቆጠር የሚጀምረው ፍርዱ የመጨረሻ ሆኖ ተፈፃሚ መሆን ይችል ከነበረበት ቀን ወይም ፍርዱ መፈፀም ጀምሮ እንደሆነ ተቀጪው ይኸው ፍርድ እንዳይፈፀምት ካመለጠበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡ ተቀጪው ፍርድ ከታገደለት በኃላ የፍርድ መታገድ ትዕዛዝ የተሻረ እንደሆነ የይርጋው ጊዜ የሚቆጠረው የቅጣቱ አፈፃፀም እንዲቀጥል ከታዘዘበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡
በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 ተደራራቢ ቅጣቶች ተወስነው እንደሆነ ለይርጋው ጊዜ አቆጣጠር መሠረት የሚሆነው ከሁሉም ከባድ የሆነው የቅጣት የይርጋ ጊዜ ነው፡፡
የቅጣትና የጥንቃቄ እርምጃ የይርጋ ዘመን መታገድ
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 226 የቅጣት ይርጋ ዘመን ታግዶ የሚቆየው
ሀ/የቅጣቱ ወይም የጥንቃቄ እርምጃው አፈፃፀም እንደ ህጉ ሊፈፀም ወይም አፈፃፀሙ ሊቀጥል ባልቻለ ጊዜ፣ ይህ መሰናክል እስከሚቆይበት ጊዜ ድረስ፣
ለ/ ተቀጪው ፍርዱ ታግዶለት፣ በአመክሮ ተፈትቶ ወይም የዕዳ መክፈያ ጊዜ ተሰጥቶ እንደሆነ የተወሰነው ጊዜ እስካላለቀ ድረስ፣
ሐ/ ነጻነትን በማሳጣት ቅጣት ወይም በሌላ የጥንቃቄ እርምጃ ለማስፈፀም ታስሮ እስከሚቆይበት ጊዜ ድረስ መሆኑ ተቀምጧል፡፡
የቅጣት የይርጋ ዘመን መቋረጥ
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 227 የቅጣት ይርጋ ዘመን የሚቋረጠው የማስፈፀም ኃላፊነት በተሰጠው ባለስለጣን ቅጣቱን ለማስፈፀም የሚደረግ ወይም ወደ ቅጣቱ አፈፀጸም የሚያመራ ተግባር በሥራ ላይ እንዲውል ከተጀመረበት ቀን አንስቶ እንደሆነ ተደንግጓል፡፡
ፍፁም የሆነ የቅጣትና የጥንቃቄ እርምጃ ይርጋ ዘመን
በወንጀል ህጉ አንቀጽ 228 ፍፁም የሆነ የቅጣትና የጥንቃቄ እርምጃ ይርጋ ዘመን፣ ለመደበኛ ሕጋዊ ቅጣት ከተወሰነው የይርጋ ዘመን /አንቀጽ 224/ በግማሽ የሚበልጥ ጊዜ ካለፈ ጠፋተኛው በዚህ ጊዜ ውስጥ ቢያንስ በፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል አስቦ በመፈጸም አደገኛ መሆኑን ካላሳየ በቀር የቅጣት ወይም የጥንቃቄ ተግባር አፈፃፀም ውሳኔ በማናቸውም ምክንያት ቢሆን ቀሪ እንደሚሆን ተቀምጧል፡፡ በዚሁ መሰረት በአንቀጽ 224 ስር የተቀመጠው ጊዜ 30ዓመት፣ 20 ዓመት፣ 10 ዓመትና 5 ዓመት ስለሆኑ 45 ዓመት፣ 30 ዓመትና 7 ዓመት ከ 6 ወር፣ በቅድመተከተል የሚሆን ይሆናል፡፡
4. ሌሎች የይርጋ ዘመን
የደንብ መተላለፍ ድርጊት የይርጋ ዘመን
በኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ አንቀጽ አንቀጽ 773 የደንብ መተላለፍ ድርጊት የይርጋ ዘመን አስመልክቶ ተደንግጓል፡፡ በዚሁ መሰረት ማናቸውም ዓይነት የደንብ መተላለፍ ድርጊት ቢሆን ክስ ሳይቀርብበት አንድ ዓመት ካለፈ፣ የተፈረደዉም ቅጣት ተፈፃሚ ሳይሆን ሁለት ዓመት ካለፈ በይርጋ ይታገዳል፡፡ የይርጋ ዘመን መጀመርን፣ መታገድን፣ መቋረጥንና ፍፁመም ማብቂያውን መጨረሻውን የሚመለከቱ ጠቅላላ ድንጋጌዎች /አንቀጽ 219 እስከ 222 እና 225 እስከ 228 ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
5. የቅጣት አይነቶች
ዋና ቅጣቶች
መቀጮ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 90 ጀምሮ የተቀመጠ ሲሆን መቀጮ ማለት በወንጀል ምክንያት የሚከፈለው ገንዘብ እንደሆነ በመጠቀስ ገቢነቱም ለመንግስት ነው በማለት ያስቀምጠዋል፡፡ መቀጮ ከብር 10 እስከ ብር 10ሺህ ሊደርስ ይችላል፡፡ ሆኖም ተቀጪው ህጋዊ ሰውነት የለው ድርጅት በሆነ ጊዜ መቀጮው ከ100 ብር እስከ 500 ሺህ ብር የሚደርስ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ንብረት መውረስ /አንቀጽ 98/ ሊያካትት ይችላል፡፡
የስራ ግዴታና ነጻነት የሚያሳጡ ቅጣቶች አንቀጽ 103-105 ከግዴታ ስራ ከሚገኘው ገቢ ተቀንሶ ለመንግስት የሚከፈል ገንዘብና የግል ነፃነትን ከመገደብ ጋር የሚወሰን የግዴታ ስራ ያካትታል፡፡
የግል ነጻነትን የሚያሳጡ ቅጣቶች ለምሳሌ ቀላል እስራት አንቀጽ 106፣ ጽኑ እስራት አንቀጽ 108፣ የሞት ቅጣት አንቀጽ 117
ተጨማሪ ቅጣቶች
በአንቀጽ 121 መሰረት ተጨማሪ ቅጣቶች ለዋነኛው ቅጣት ተደራቢ ወይም ማሟያ ተደረገው የሚወሰኑ ቅጣት ነው፡፡ ለምሳሌ ማስጠንቀቅያ፣ ወቀሳ፣ ተግሣፅ፣ ጥፋተኛው የሚጠይቀው ይቅርታ አንቀጽ 122፣ የመብት መሻር አንቀጽ 123 ናቸው፡፡
የጥንቃቄ እርምጃዎች
በአንቀጽ 157 መሰረት ዕድሜው ከዘጠኝ እስከ አስራ አምስት ዓመት የሆነ ወጣት በወንጀል ሕግ ከተመለከቱት ወንጀሎች አንዱን ፈፀሞ በተገኘ ጊዜ እንደሆነ /አንቀጽ 53 ወጣት ወንጀል አድራዎች ላይ የሚፈፀሙ ሉዩ ድንጋጌዎች/ ፍርድ ቤቱ የህጉን ጠቅላላ ድንጋጌዎች ከመከተልና ከነገሩም ልዩ ግብ ለመድረስ /አንቀጽ 55/ አስፈላጊ ሲሆን ነገሩን ለመረዳት ተገቢ የሆነው ምርመራ እንዲደረግ ካዘዘ በኋላ /አንቀጽ 54 ከተለያዩ የጥንቃቄ እርምጃዎች አንዱን እንደሚያዝ ተቀምጧል፡፡ እርምጃዎቹም ሕክምና ወደሚገኝበት ተቋም መላክ /አንቀጽ 158/ ፣ ቂጥጥር በማድረግ የሚሰጥ ትምህርት /አንቀጽ 159/፣ ተግሳፅና ወቀሳ /አንቀጽ 160/፣ በትምህርት ቤት ወይም በመኖርያ ቤት ተወስኖ እንዲቆይ ማድረግ /አንቀጽ 161/ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
Popular posts
-
የፍትሐዊ ውሳኔ አሰጣጥ ፥ ከስነ ስርዓት አካሄድ አንጻር ውሳኔ ሰጪ የሆነ የመንግስት አካል በቅን ልቦና ተመርቶ አድሎአዊ ያልሆነ ውሳኔ መስጠትና ከሁሉም በላይ በውሳኔው መብቱ ወይም ጥቅሙ ሊነካ ለሚች...
-
Legal Terms used in Daily Routine & their meanings: ============================= AB INITIO: "from the beginning" AB INITIO...
-
አስተዳደራዊ ድንጋጌ የማውጣት ስልጣን ባህርያትና የስልጣን ምንጭ አስተዳደራዊ ድንጋጌ ከህግ አውጭው በተሰጠ የውክልና ስልጣን ገደብ ውስጥ በስራ አስፈፃሚው የመንግስት አካል የሚወጣ የበታች ህግ (subordinate legis...
-
አንድን ድርጊት መፈፀም ወይም አለመፈፀም ወንጀል የሚሆነው በመንግስት /በዐቃቤ ሕግ/ የሚያስከስስና በህግ የሚያስቀጣ ሲሆን ነዉ፡፡ ወንጀል የሚባለው አንድ ሰው ለህገወጥ ድርጊቱ በመንግስት የሚቀጣ ሆኖ በግልፅ ህግን የመጣስ...
-
የከሳሽነት ብቃት ‘አንድን የአስተዳደር ተግባር በፍርድ ቤት ወይም በሌላ የዳኝነት ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መሞገት የሚችለው ማነው?’ የሚለው ጥያቄ በአስተዳደር ህግ ውስጥ መልስ አሁንም ድረስ መቋጫ የሌለው አን...
-
The Constitution of Ethiopia The so-called "Ethiopian constitution" is the "constitution of the people" of Ethiopia. I ...
-
ታሳሪዎቹ እነ ጀዋር ሞሐመድ በግል ሐኪም እንዲታከሙ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ተወስኗል፡፡ ተከሳሾቹ በወህኒ ቤት በፈለጉት ሐኪም እንዲታከሙ ነው ፍርድ ቤቱ የወሰነው፡፡ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ችሎት ውሳኔውን የሰጠው የከ...
-
EFFECTS OF MARRIAGE Section 1. General Rules Article 40. – Various Forms of Marriage Equivalent. 1) Marriage produces the same legal effec...
-
The International Criminal Court After countries throw off oppressive regimes or emerge from civil war they face a period of (what we now ca...
Recent Posts
-
ከቤተልሔም እስከ ግብፅ - *በመ/ር ዓለማየሁ ሀብቴ* *በስመ **አብ **ወወልድ **ወመንፈስ **ቅዱስ **አሐዱ **አምላክ **አሜን!* ክቡራንና ክቡራት የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፣ እንደምን ከረማችሁ? ልዑል እግዚአብሔር በቸርነቱ ለዚህች ሰዓት ስላደረሰን ስሙ ከዘላለም ...
-
-
ሁሉም ሸማች ሆኖ ሳለ ያልተገባ የምርቶች ዋጋ ጭማሪ ለምን? - በገበያ መር ኢኮኖሚ ገበያውን የሚቆጣጠሩት ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ይልቅ ሁለቱ ዋና ዋና ኃይሎች (Market forces) ፍላጎትና አቅርቦት እንደሆኑ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ በነፃ ኢኮኖሚ መርህ አምራቾች ምን እና በምን ያህል ...
-
The genocidal campaign against the civil society of the people of Tigray has continued with the war and the plundering of the Tigreans' property and the massacre of the Tigrayans. The oppression of the people and the rape of women, mothers in Tigray and so on. It is still happening. This is the angle of injustice in Tigray. What confuses me? Who can be held accountable for all this? - *The genocidal campaign against the civil society of the people of Tigray has continued with the war and the plundering of the Tigreans' property and the...
-
-
HOPE HOPE HOPE , I would Hope Not to Die...... - Such a Calmness that I found in your eyes, can't let me go, can't let me sleep, can't let me die.... ...
-
-
-
Rethinking Evidence and recording depositions. - We are living in a world where Artificial intelligence is fastly developing. One key area which the judges are having trouble with is to distinguish betwee...
-
Dessie Dalga _ደሴ ዳልጋ :የወጣቶች ተሳትፎ ከገበታ ባሻገር - - Dessie Dalga _ደሴ ዳልጋ: dalgadessie83.blogspot.com/ Youth participation is the active engagement of young people throughout their own communities. It i...
-
With the support of Allah we have done it again - With the support of Allah we have done it again Alhamdulillahi robil alamin became an anthem yesterday for the entire darul-hikmah / yemkem muslim umm...
-
የነፃነቱ ታላቅ ባለድርሻ - የነፃነቱ ታላቅ ባለድርሻ Negotiating A Lion's Share of Freedom: I am so impressed when a relatively new author writes such a compelling and intriguing life story, ...
-
Life - I feel like I have neglected my blog but life happens and it was more exciting to write while we were waiting for our son to come home. Now he is home and ...
-
-
-
"ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው" ቅ.ዮሐንስ ራእይ ም 15፡3-4 - *በሻሌ ንቡ ቅ/ሚካኤል ቅ/እስጢፋኖስ ወአባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ቤተክርስቲያን* *አሁን አገልግሎት እየሰጠ ያለው ቤተክርስቲያን* *ከቤተመቅደሱ የተቆረጠው ማር ህዳር 12 ቀን 2006 ዓ.ም የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል ሲ...
-
New Infographic: Best Day to Send Email 2013 - Exactly one year after publishing our first *“Best Time to Send Email”* infographic, we bring you an extended update with exciting additional email data a...
-
-
A Year Home - It's a bit strange to sit down and have the time to write again. This day is monumental in our lives and one that has brought me back to making the time to...
-
Day 1 of our time in Ethiopia - After 35 hours of travel, we arrived at the Addis Ababa airport very late Thursday evening. Exhausted, we then waited in the tourist visa line, exchanged s...
-
A Visit to the Village - It's customary for the bride & groom to visit the family's home village after the wedding. It's sorta like saying "thank you" for coming to the wedding...
-
-
-
LikeBtn
Type
አስተማሪ የሆኑት የችሎት ድራማ ቪዲዮዎች
DOCUMENT & FILES
Criminal Procedure Code 6/2013 PDF by ሕግ እና ፍትህ on Scribd

