1 Apr 2018

አዋጅ ቁጥር 916/2008 (በአዋጅ ቁጥር 942/2008 እና 1084/2010 እንደተሻሻለ) አንቀጽ 5 እና 37 መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል።



የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 916/2008 (በአዋጅ ቁጥር 942/2008 እና 1084/2010 እንደተሻሻለ) አንቀጽ 5 እና 37 መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል።
  1. አጅር ርዕስ ይህ ደንብ "የሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 426/2010" ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።
  2. ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፦
    1. "ቤተ መንግሥት" ማለት የመንግሥትና የሀገር መሪዎች የሚሰሩበትና የሚኖሩበት ማንኛውም ስፍራ ሲሆን፤ ሁለቱም ቤተ መንግሥቶች፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግቢና የቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ ቪአይፒ ተርሚናልን፤ እንዲሁም የጠቅላይ ሚንስትሩን፣ የርዕሰ ብሔሩንና የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጊዜያዊ የስራና ማረፊያ ቦታዎችን ያጠቃልላል፤
    2. የመሪዎች ቤተሰብ" ማለት የጠቅላይ የርዕሰ ብሄሩና የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትዳር አጋሮች እና በስራቸው የሚተዳደሩ እስከ 21 ዓመት የሆናቸው ልጆቻቸውን ያጠቃልላል፤
  3. “ግቢ” ማለት በጥበቃ ኃይሉ ጥበቃ የሚሸፈን ሕንጻ ዙሪያ፣ በውስጥ ያሉትን ቢሮዎች፣ ወደ ግቢ የሚገቡና የሚወጡ ማናቸውንም ሰዎች፣ ቁሶችን፣ ቴክኖሎጂዎችን፣ በግቢ ውስጥ የሚገኙ ሀብቶችንና መሠረተ ልማቶችን ያጠቃልላል፤
  4. “አስፈላጊ ቴክኖሎጂ" ማለት በዚህ ደንብ የጥበቃ ሸፋን ያገኙ መሪዎችንና የቤተሰቦቻቻውን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያግዝ፣ ተሽሸከርካሪ፣ ሰው አልባ አውሮፕላን፣ ሄሊኮፕተር፣ ደረጃውን የጠበቀ ትጥቅ፣ እንስሳትና ሌሎች የኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂን ያጠቃልላል፤
  5. “መለዮ ለባሽ ኃይል" ማለት በዋናነት የጥበቃ፣ ፍተሻና እጀባ ሥራ የሚሰራው የታጠቀ ኃይል ነው፡
  6. “የመንግሥትና የሀገር መሪዎች" ማለት እንደቅደም ተከተሉ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ርዕሰ ብሔር ነው፤
  7. “ድጋፍ ሰጪ ኃይል" ማለት የተለያየ የተፈጥሮ ሳይንስ፣ የማህበራዊ ሳይንስና ቴክኒካዊ እውቀት ያላቸው ሙያተኞች የተሰባሰቡበት ኃይል ነው፤
  8. “ኦፕሬሽናል" ማለት የዕዝ ሰንሰለት እና በዚህ ደንብ የተደነገጉትን ዋና ተግባራት ያጠቃልላል፤
  9. “አስተዳደራዊ ሥራዎች" ማለት ከሰው ኃይል አስተዳደር፣ ከበጀት አስተዳደርና ሌሎች ተዛማጅ ስራዎች ጋር የተያያዘ ሥራ ነው፤
  10. “ሚኒስቴር" ወይም "ሚኒስትር” ማለት እንደቅደም ተከተሉ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴርና ሚኒስትር ነው፤
  11. ማንኛውም በወንድ ፆታ የተገለፀው የሴትንም ፆታ ይጨምራል።
  12. መቋቋም
    1. የሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል (ከዚህ በኋላ “የጥበቃ ኃይል" እየተባለ የሚጠራ) የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል።
    2. የጥበቃ ኃይሉ ለኦፕሬሽናል ሥራዎች ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሲሆን፤ ለአስተዳደራዊ ጉዳዮች ሲባል ተጠሪነቱ ለሚኒስቴሩ ይሆናል።
  13. ዋና መስሪያ ቤት
የጥበቃ ኃይሉ ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ በማንኛውም ስፍራ ጊዜያዊ ጽሕፈት ቤት ሊኖረው ይችላል።
  1. ዓላማ የጥበቃ ኃይሉ ዓላማ አስፈላጊ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችለውን ቅደመ ዝግጅት በማድረግ የመንግሥትና የሀገር መሪዎችን ደህንነትና ቤተ መንግሥትን መጠበቅ ነው።
  2. የጥበቃ ኃይሉ ተግባራትና ላፊነት የጥበቃ ኃይሉ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፦
    1. የቤተ መንግሥት ጥበቃ የአሠራር ሥርዓትና ስታንዳርድ አዘጋጅቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀርባል ሲፀድቅም በኃላፊነት ይፈጽማል፤
    2. የሰው ኃይል ምልመላ፣ ስልጠና፣ ወቅታዊ ግምገማና ዝውውር ወይም ስንብት መመሪያዎችን አዘጋጅቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያቀርባል ሲጸድቅም በኃላፊነት ያስፈጽማል፤
    3. ከሚኒስቴሩና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት አስፈላጊ የሰው ኃይል ይመለምላል፣ ያሰለጥናል ይቀጥራል፣ ያሰማራል፤
    4. ለተልዕኮው አፈጻጸም የሚያስፈልጉት ማናቸውም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ፤ ቁሳቁስ፣ ትጥቅና አስፈላጊ ቴክኖሎጂ ይታጠቃል፤
    5. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (4) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የሚስፈልገውን ድጋፍ በጊዜያዊነት ከሌሎች ተቋማት ያገኛል፤
    6. የጠቅላይ ሚኒስትሩንና የቤተሰቡን፣ እንዲሁም የርዕሰ ብሔሩንና የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩንና ቤተሰቦቻቸውን ድህንነት ያረጋግጣል፤
    7. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (6) የተጠቀሰው እንደጠበቀ ሆኖ የደህንነት ጥበቃው የቀድሞ ርዕሰ ብሔርን፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርን፣ የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርንና ቤተሰቦቻቸውንም የሚያካትት ሲሆን፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የተሾሙትን አያካትትም፤
    8. ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገቡ የሌሎች ሀገራት የመንግሥትና የሀገር መሪዎች፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ኃላፊዎችን እንዲሁም በዚህ ደረጃ ለሚታዩ ሰዎች ጥበቃ ያደርጋል፤
    9. የክብር ዘብ አገልግሎት ይሰጣል፤
    10. ልዩ ተልዕኮውን ታሳቢ በማድረግ ለተልዕኮ አፈጻጸም የሚያስፈልጉትን አደረጃጀቶች አጥንቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀርባል፤ ሲጸድቅም
በኃላፊነት ያስፈጽማል፤
    1. የሀገርና የመንግሥት መሪዎችን ደህንነትና ቤተ መንግሥትን ለመጠበቅ አስፈላጊ እርምጃ ይወስዳል፤
    2. የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ሃ ውል ይዋዋላል፣ በራሱ ስም ይከሳል፣ ይከሰሳል፤
    3. ዓላማውን ለማስፈጸም የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል።
  1. የጥበቃ ኃይሉ አደረጃጀት ፦ የጥበቃ ሐይሉ፡-
    1. በመንግሥት የሚሾሙ አዛዥና ምክትል አዛዦች፤
    2. እንዲሁም አስፈላጊ መለዮ ለባሽና ሌሎች ድጋፍ ሰጪ ሲቪል ሠራተኞች ይኖሩታል።
  2. የአዛዡ ፡ ሥልጣንና ተግባር አዛዡ ለኦፕሬሽናል ጉዳዮች ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፤ ለአስተዳደራዊ ጉዳዮች ሲባል ተጠሪነቱ ለሚኒስትሩ ሆኖ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፦
    1. የጥበቃ ኃይሉን ሥራዎች ይመራል፣ ያስተዳድራል፤ ያዛል፤
    2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) አጠቃላይ አገላለጽ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አዛዡ፦
ሀ) በዚህ ደንብ አንቀጽ 6 የተመለከቱትን የጥበቃ ኃይሉን ሥልጣንና ተግባር በሥራ ላይ ያውላል፤
ለ) በሚወጡ መመሪያዎች፣ የአሠራር ሥርዓቶችና ስታንዳርዶች መሠረት ስራውን በበላይነት ያስተባብራል፤
ሐ) እንደ የሁኔታው አዳዲስ አሰራሮችንና አደራጃጀቶችን እያጠና ለውሣኔ ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፤
መ) የጥበቃ ኃይሉ ሠራተኞች የሰራተኞቹን ስብጥር ታሳቢ አድርጎ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚፀድቅ መመሪያ መሠረት ይቀጥራል፣ያስተዳድራል፤ ሠ) የጥበቃ ኃይሉን ዓመታዊ የስራ ዕቅድና በጀት አዘጋጅቶ ለሚኒስትሩ ያቀርባል፣ በመንግሥት ሲፈቀድም በስራ ላይ ያውላል፤
ረ) በጥበቃ ኃይሉ በጀትና የሥራ ዕቅድ መሠረት ክፍያዎችን ያፀድቃል፤ ይፈጽማል፤
ሰ) ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚደርጉ ግንኙነቶች ሁሉ የጥበቃ ኃይሉን ይወክላል፤
ሸ) የጥበቃ ኃይሉ ከኦፕሬሽናል ውጭ ያሉትን የሥራ ክንውኖችና የሂሣብ ሪፖርቶች አዘጋጅቶ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል፡፡
3. አዛዡ ለሥራ ቅልጥፍና ሲባል ከስልጣኑና ተግባሩ በከፊል ለየጥበቃ ኃይሉ ምክትል አዛገፐችና ሌሎች ሠራተኞች በውክልና ሊሰጥ ይችላል።
  1. የምክትል አዛዡ ሥልጣንና ተግባር ምክትል አዛኙ ተጠሪነቱ ለአዛዡ ሆኖ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፦
    1. በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት በሚጸድቅ የስልጣን ውክልና መመሪያ መሰረት የተሰጡ ሥልጣንና ተግባራትን ያከናዉናል፤
    2. ከአዛዡ ተለይተው የሚሰጡ ሥልጣንና ተግባራትን ያከናውናል፤
    3. አዛዡ በሌለበት ጊዜ የሥልጣን ውክልና ያልተሰጠ እንደሆነ በማዕረግ ቅድሚያ ያለው ምክትል አዛዥ በዚህ ደንብ ለአዛዥ የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባራት በኃላፊነት ያከናውናል።
  2. የጥበቃ ኃይሉ በጀት የጥበቃ ሐይሉ በጀት በመንግሥት ይመደባል።
  3. ስለ ሒሣብ መዛግብት
    1. የጥበቃ ኃይሉ የተሟላና ትክክለኛ የሆኑ የሒሣብ መዛግብት ይይዛል።
    2. የጥበቃ ኃይሉ የሒሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚሰይመው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ፡፡
  4. የመተባበር ግዴታ
    1. ማንኛውም የፌደራል ወይም የክልል የጸጥታናሕግ አስፈጻሚ አካል እና ሌላ ተቋም በዚህ ደንብ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማስፈጸም ሲባል ከጥበቃ ኃይሉ ለሚቀርብለት የትብብር ጥያቄ የመተባበር ግዴታ አለበት።
    2. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (1) የተገለጸው ትብበር፣ የሰው ኃይል፣ ተሽከርካሪ፣ ቢሮ፣ መረጃ ወይም ሌላ ቁሳዊና ኢቁሳዊ ሀብት ሊሆን ይችላል።
  5. ስለ መብት መተላለፍ
ከቤተ መንግሥት ጥበቃ፤ እጀባና የክብር ዘብ አገልግሎት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ማናቸውም ቁሳዊና ሌሎች ተዛማጅ ሀብቶች በዚህ ደንብ መሠረት ለጥበቃ ኃይሉ
ተላልፏል።

No comments:

Post a Comment

Popular posts

Recent Posts

LikeBtn

Type

አስተማሪ የሆኑት የችሎት ድራማ ቪዲዮዎች

DOCUMENT & FILES

Criminal Procedure Code 6/2013 PDF by ሕግ እና ፍትህ on Scribd