8 Aug 2020

ነቄ እጅ

ነቄ እጅ
ተከሳሽ በስርቆት ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ የእስራት ቅጣት ተወሰነበት፡፡ ወደ ማረሚያ ከመላኩ በፊት የተከሳሽ ጠበቃ ድንገት ከተቀመጠበት ተነስቶ ድምፁን በማጉላት “ጌታዬ!” ብሎ አቤቱታ ማሰማት ጀመረ፡፡
“ጌታዬ! እርግጥ ነው የደንበኛዬ እጅ ክፍት በነበረ የመደብር መስኮት ዘው ብሎ ገብቶ አንዳንድ ጠቃሚ ዕቃዎችን ይዞ ወጥቷል፡፡ ያለ ጥርጥር የደንበኛዬ ቀኝ እጅ ወንጀል ሰርቷል፡፡ ሊቀጣም ይገባዋል፡፡ ይሁን እንጂ ወንጀሉን የፈጸመው እጅ የተከሳሽ የራሱ ቢሆንም እጁ ግን ተከሳሹ ራሱ አይደለም፡፡ ጌታዬ! ቀኝ እጅ ለሰራው ወንጀል ተከሳሹን ማረሚያ መላክ ፍትሐዊ ነው?” ጠበቃው ለጥያቄው ምላሽ እየተጠባበቀ በእርጋታ ተቀመጠ፡፡ የተከበሩት ዳኛ ጠበቃው ጨዋታ እንዳማረው ስለገባቸው በፊናቸው የሚከተለውን ትዕዛዝ ሰጡ፡፡
“ጥሩ! ጠበቃው ያለውን ሰምተናል፡፡ ስለሆነም የተከሳሽ ቀኝ እጅ ማረሚያ እንዲላክ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡ ተከሳሽ ከፈለገ እጁን ተከትሎት ወደ ማረሚያ ይሂድ፡፡”
የልቡ የደረሰለት ጠበቃ የተከሳሹን አርተፊሻል እጅ አውልቆ ጠረጴዛ ላይ በማስቀመጥ ተከሳሹን ይዞት ወጥቷል፡፡

No comments:

Post a Comment

Popular posts

Recent Posts

LikeBtn

Type

አስተማሪ የሆኑት የችሎት ድራማ ቪዲዮዎች

DOCUMENT & FILES

Criminal Procedure Code 6/2013 PDF by ሕግ እና ፍትህ on Scribd