10 Sept 2020

የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ መቁረጥ እና ሕጋዊነቱ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064



የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ መቁረጥ እና ሕጋዊነቱ


የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064


 የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064

በሌላ በኩል ደግሞ በመንግሥት ባለቤትነት ሥር የሚተዳደሩ የልማት ድርጅቶች ሥር የሚሰሩ ሠራተኞች የሚተዳደሩበት ህግ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 ይሰኛል፡፡ እነዚህ ሠራተኞች በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ከመንግሥት አስተዳደራዊ ቁጥጥር ውጪ ባለመሆናቸው እና ቀጣሪያቸው መንግሥት በመሆኑ ለዚህ ጽሑፍ አላማ ሲባል የመንግሥት ሠራተኛ ልንላቸው እንችላለን፡፡

የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ የሚቆረጠው በምን አግባብ ነው?

የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 በፌደራል መንግሥቱ ሥር ተቀጥረው የሚሰሩ ሠራተኞች የሚተዳደሩበት ህግ ነው፡፡ በዚህ ህግ ላይ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ በምን አኳኋን ሊቆረጥ እንደሚችል በግልፅ አስቀምጧል፡፡ የአዋጁ አንቀፅ 9 (2) የደመወዝ ክፍያ በሚለው ርዕስ እንዲህ ይነበባል፡፡

የማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ፣

ሀ)   ሠራተኛው ስምምነቱን በጽሑፍ ሲገልጽ፣

ለ)   በፍርድ ቤት ትዕዛዝ፣

ሐ)   በሕግ በተደነገገው መሠረት፣

ካልሆነ በስተቀር ሊያዝ ወይም ሊቆረጥ አይችልም፡፡

አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ደግሞ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሚተዳደሩበት ህግ ነው ይህም የህግ ማዕቀፍ ከቀደመው ጋር በተመሳሳይ የሠራተኛን ደመወዝ አሰሪው ሊቆርጥ የሚችለው ሠራተኛው በጽሑፍ ሲስማማ እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡

ከላይ ካሉት ድንጋጌዎች መረዳት የምንችለው አንድ የመንግሥት ሠራተኛ የደሞዜ ይሄን ያህን ፐርሰንት ይቆረጥብኝ ብሎ በጽሑፍ ወይም በፊርማው ስምምነቱን ካላረጋገጠ ሊቆረጥበት እንደማይችል ነው፡፡ የመንግሥት መ/ቤቶች ለተለያዩ መዋጮዎች የሠራተኛውን ደመወዝ ሲፈልጉ ምን ያህሉን ሠራተኛ "ደመወዝህን ልቆርጥብህ ስለሆነ ትስማማለህ ወይ?" ብለው ይጠይቃሉ? ይህም ቢሆን መስማማቱ ብቻ አይደለምና ምን ያህሉ ነው ስምምነቱን በፊርማው አረጋግጦ ደሞዙ የሚቆረጠው? ጭራሽ ሳይሰሙ እና ሳያውቁ ደሞዛቸው የተቆረጠባቸውስ የሉም? ወይ የሚሉትን እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ለአንባቢ እተዋለው፡፡ 

አቶ አንበሴ የሚሰሩት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሚሰኝ የመንግሥት የልማት ድርጅት ውስጥ ነው፡፡ ለዚህ ጽሑፍ ሲባል  ከሳቸው ጋር ባደረኩት ቆይታ ከፍቃዳቸው ውጪ እንዴት ደሞዛቸው እንደተቆረጠ የሚከተለውን ብለዋል፡- "እንኳን ደሞዛችሁ ሊቆረጥ ነው ፈቃደኛነታችሁን በጽሑፍ ግለፁ ተብለን ልንጠየቅ ቀርቶ ምንም አይነት ውይይት አላደረግንም፡፡ እንዳውም እንደሌላ ሰው በዜና ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች እና አመራሮች ለገበታ ለሃገር መርሃግብር የአንድ ወር ደሞዛቸውን በማዋጣት 102,000,000 (አንድ መቶ ሁለት ሚሊዮን) ብር ገቢ አደረጉ የሚል ዜና ሰማን፡፡" ከላይ ከጠቀስናቸው የህግ ድንጋጌዎች አንፃር ስንመዝነው ይህ አካሄድ ሙሉ ለሙሉ ከህግ ውጪ የሆነ ነው፡፡ የፕሮጀክቱ አላማም ከፍቃዳቸው ውጪ ከሰዎች ጉሮሮ ገንዘብ መንጠቅ ነው ብዬ አላምንም፡፡

ደሞዙ ከፍቃዱ ውጪ የተቆረጠበት የመንግሥት ሠራተኛ ምን ማድረግ ይችላል

የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀፅ 79 የመንግሥት ሠራተኞች መብቴ ተጣሰ ብለው የሚያቀርቧቸውን የስራ ክርክር ክሶችን የሚዳኝ የአስተዳደር ፍርድ ቤት ተቋቁሟል፡፡ ይህ ፍርድ ቤት ከሚያያቸው ጉዳዮች መካከል ከህግ ውጪ የደመወዝ መያዝ ወይም መቆረጥ አንዱ ነው፡፡ ስለሆነም ከላይ በተገለፀው አኳሃን በጽሑፍ ስምምነቱን ሳይገልፅ ደሞዙ የተቆረጠበት የመንግሥት ሠራተኛ ቀጣሪውን መ/ቤት በአስተዳደር ፍ/ቤት ቀርቦ መክሰስ እና የተቆረጠበትን ደሞዙን ማስመለስ እንደሚችል ህጉ ያስቀምጣል፡፡ በተመሳሳይ ለመንግሥት የልማት ድርጅት ሠራተኞችም በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የስራ ክርክር ጉዳዮችን የማየት ስልጣን በተሰጠው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመቅረብ ከፈቃዴ ውጪ ደሞዜ ተቆርጧል የሚል ክስ አቅርቦ ገንዘቡን ማስመለስ ይችላል፡፡

 

ማጠቃለያ

የመንግሥት ሃላፊዎች የሚወስኗቸው እያንዳንዱ ውሳኔዎች ህግን መሰረት ያደረገ መሆኑን ማረጋገጥ ለሚመሩት ተቋምም ሆነ ለሚያስተዳድሩት ሠራተኛ ደህንነት መጠበቅ እጅግ ወሳኝ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በአንዳንድ ሃገራት በዓላትን አስታኮ በቦነስ መልክ ሠራተኞች የሚያወጧቸውን ወጪዎች እንዲሸፍኑ የ2 እና 3 ወር ደመወዝ መስጠት የተለመደ አሰራር ነው ይሁን እንጂ በእኛ ሃገር ነባራዊ ሁኔታ የተለያዩ ምክንያቶችን እየደረደሩ የሠራተኛውን ደመወዝ ፈቃዱን ሳይጠይቁ መቁረጥ ከህግ ውጪ ከመሆኑም ባሻገር በስራው እርካታ የራቀውን ሠራተኛ ከመፍጠር አልፎ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚያመጣው አሉታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል ሠራተኛውም በመሪዎች ተፅዕኖ ሥር ወድቆ በጀርባ ሆኖ ከማጉረምረም ይልቅ መብቱን እና ግዴታውን ጠንቅቆ በማወቅ በህግ ለተሰጠው መብት መታገል እና ግዴታውን መወጣት ይኖርበታል፡፡

1 comment:

Popular posts

Recent Posts

LikeBtn

Type

አስተማሪ የሆኑት የችሎት ድራማ ቪዲዮዎች

DOCUMENT & FILES

Criminal Procedure Code 6/2013 PDF by ሕግ እና ፍትህ on Scribd