ከምክንያታዊ ጥርጣሬ የፀዳ
• በወንጀል ጉዳይ ተከሳሽ ጥፋተኛ እንዲባል ጠንካራና የማያሻማ ማስረጃ እንደሚያስፈልግ የሚያስገነዝብ የወንጀል ህግ የማስረጃ ምዘና መርህ
የወንጀል ክስ የማስረጃ ምዘና መርህ ከምክንያታዊ ጥርጣሬ የፀዳ /Beyond reasonable doubt/የሚል ሲ
ሆን በዚህ የማስረጃ አመዛዘን
መርህ መሠረት በወንጀል ጥፋተኛ ለማሰኘት ጠንካራና የማያሻማ ማስረጃ የሚፈለግ ሲሆን የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅን መሠረት የሚያደርግ ክስ በባሕሪይው ከዲሲፕሊን እርምጃ ጋር እጅጉን የተቆራኘ በመሆኑ እንደማንኛውም የዲሲፕሊን ክስ ተፈፃሚነት የሚኖረው የማስረጃ ምዘና መርህ ከወንጀል ክስ የማስረጃ ምዘና ላላ ያለ ነው፡፡ በመሆኑም በወንጀል ተከሶ ነፃ የሚወጣ ሠራተኛ በዲሲፕሊን ቢከሠስ አጥፊ ሆኖ የመገኘት ዕድሉ ሠፊ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት ከወንጀል ክስ ነፃ በመውጣት ብቻ አንድ ሠራተኛ ወደ ቀድሞ ሥራ ልመለስ ይገባል በማለት የሚያቀርበው ጥያቄ የሕግ ድጋፍ አይኖረውም፡፡ ስለሆነም የሠራተኛው ጥያቄ ሊስተናገድ የሚገባው ላላ ያለ የማስረጃ ምዘና መሠረት ተደርጎ ለአድራጎቱ ተጠያቂ ሆኖ መገኘት አለመገኘቱን መሠረት በማድረግ ነው፡፡

Read and Experience it.
ReplyDelete