የስልጣን ክፍፍል በአገራችን ህገ መንግስታዊ መርህ ሲሆን ህግ አውጭው፤ ህግ ተርጓሚውና ህግ አስፈፃሚው ያላቸውን ስልጣን ከፋፍሎ
የስልጣን ክፍፍል
የስልጣን ክፍፍል በአገራችን ህገ መንግስታዊ መርህ ሲሆን ህግ አውጭው፤ ህግ ተርጓሚውና ህግ አስፈፃሚው ያላቸውን ስልጣን ከፋፍሎ ያስቀምጣል፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ መርህ በተቃራኒ የአስተዳደር ህግ ከተግባራዊ ምክንያቶች የተነሳ ስራ አስፈፃሚው አካል ሕግ ከማስፈፀም ስልጣኑ በተጨማሪ ህግ የማውጣትና ህግ የመተርጐም ተግባራትን እንዲያከናውን በልዩ ሁኔታ ይፈቅዳል፡፡ እነዚህ ተደራራቢ ስልጣናት የመንግስት አስተዳደርን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ በልዩ ሁኔታ የተሰጡ እንጂ በመርህ ደረጃ ከስልጣን ክፍፍል መሰረተ ሀሳብ ጋር ይጋጫሉ፡፡ ስለሆነም የህገ መንግስቱ የስልጣን ክፍፍል መርህ የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ደንብና መመሪያ የማውጣት እና ዳኝነታዊ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን በአፈፃፀም ረገድ በጠባቡ እንዲተረጐም በማድረግ የዚህ ስልጣናቸው ገደብ ሆኖ ያገለግላል፡፡
ይኸው መርህ ፍርድ ቤቶች ሚናቸው እስከየት ድረስ እንደሚዘልቅ ይወስናል፡፡ መደበኛ ፍ/ቤት በህግ ተለይተው በታወቁ የምርመራ ምክንያቶች ስልጣን ካልተሰጠው በስተቀር በስልጣን ውስጥ የተፈፀመ ድርጊት ከማረም መቆጠብ ይኖርበታል፡፡ ፍ/ቤቶች በስልጣን ውስጥ የተፈፀመ ድርጊትን የሚያርሙ ከሆነ በስራ አስፈፃሚው ስልጣን ጣልቃ በመግባት የስልጣን ክፍፍል መርህን ይጥሳሉ፡፡

No comments:
Post a Comment