የፍትህና የህግ ጥናትና ምርምር ዘርፍ
የፍትህና የህግ ጥናትና ምርምር ዘርፍ ከሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል የጥናትና ምርምር ስራ አንዱና ዋንኛው ነው፡፡
የፍትሕና የሕግ ሥርዓት ጥናትና ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር የጥናትና ምርምር ስራዎችን ለመስራት የተደራጀ ሲሆን፣ በስሩ ሶስት ዳይሬክቶሬቶች የያዘና ተጠሪነቱም ለኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ሲሆን የሚከተሉት ተግባራት ያከናዉናል፡-
- • ዳይሬክተሩ በሚሰጠው ውክልና መሠረት ዳይሬክተሩ ሳይኖር የሱን ሥራ ተክቶ ይሠራል፣
- • የሕግና ፍትህ ምርምሩን የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ መርሃ ግብርና በጀት አዘጋጅቶ ለዳሬክተሩ ያቀርባል፣ሲፈቅድም በሥራ ላይ ያውላል፣
- • የቢሮውን ተግባር ያቅዳል ፣በሥሩ የተደረጁትን ዲፓርትመንቶች ሥራ በበላይነት ይመራል፣ያስተባብራል፣ይቆጣጠራል፣
- • የሚካሄደው ምርምርና በአገሪቷ ውስጥ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትን ለማፋጠን በሚያስችል መልኩ እንዲነደፉ ያደርጋል፣
- • የፐብሊክ ሕግ፣ የሲቪልሕግ እና የፍትሕ ሥርዓት ጥናት ጥናትና ምርምር ስራዎችን ማቀድ፣ ማስተባበር፣ መምራት እና መደገፍ፣
- • የፍትሃብሄር ፍትህ፣ የወንጀል ፍትህ እና የአስተዳደር ፍትህ ተቋማት አፈጻጸም ከቅልጥፍና፣ ውጤታማነትና ተደራሽነት፣ ፍትሃዊነት፣ ምላሽ ሰጭነት፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት አንጻር የሚገኝበትን ሁኔታ በማጥናት አፈጻጸማቸውን ለማጠናከር የሚረዱ የማሻሻያ ሃሳቦችን ማቅረብ፤
- • በሕግ ትምህርት እና ሥልጠና ሥርዓቱ ላይ ጥናት በማካሄድ በእውቀቱ፣ በክህሎቱ፣ በአመለካከቱ፣ እንዲሁም በሥነ ምግባሩ ብቁ የሆነ አመራር እና ባለሞያ ለማፍራት የሚቻልበትን ሁኔታ ለማጠናከር የሚያግዙ ሃሳቦችን ማመንጨት፤
- • የፍትህ ዘርፉ ለኪራይ ሰብሳቢነት ያለውን ተጋላጭነት በጥናት በመገምገም በዘርፉ ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመከላከል የሚያግዙ የመፍትሄ ሃሳቦችን መጠቆም፤
- • በባህላዊ የፍትህ ተቋማት እና በአሰራራቸው ላይ ጥናት በማካሄድ ከመደበኛው የፍትህ ሥርዓት ጋር ተጣጥመው ስራ ላይ እንዲውሉ ለማድረግ የሚረዱ ምክረ ሃሳቦችን ማቅረብ፤
- • የፍትህ ሥርአቱን በሚመለከት የማማከር አገልግሎት መስጠት፣
- • የፍትህ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራር ለማጠናከር የሚረዱ ስልቶች መለየት፤
- • አስፈላጊ የሆኑ ጥናትና ምርምር ውጤቶችን እንዲታተሙና እንዲሰራጩ ውሳኔ ይሠጣል፣
- • በሥሩ የሚገኙ የጥናትና ምርምር የስራ ክፍሎችን ጥረት ለማስተባበር፣ጥንካሬና ድክመቶቻቸውን ለመገምገምና በጋራም መፍትሄ ለመስጠት የስራ ክፍሎችን ስብሰባ ይመራል፣
- • በስሩ ያሉ ዲፓርትመንቶችን ባለሙያዎች የሙያ ብቃታቸውን ለማዳበርና ከአዳዲስ ጽንሰ ሐሳቦች ጋር እንዲተዋወቁ አስፈላጊውን ሥልጠና እንዲያገኙ ያደርጋል፣
- • የዲፓርትመንቶችን ውጤት ተኮር የዕቅድ አፈጻጸም ምዘና ያከናውናል፣
- • በየዲፓርትመንቶቹ ያሉትን ሰራተኞች በ1 ለ 5 ማደራጀት ፣የውይይታቸውን ሪፖርት መከታተል እና በውይይቱ ለተነሱ ጥያቄች በአሰራር መፍትሔ መስጠት፣
- • ከየዲፓርትመንቶቹ የሚቀርቡትን የሕግ ጥናት እና ምርምሮች የሚገመግም የቴክኒክ ኮሚቴ ያዋቅራል ፣በበላይነት ስራውን ይቆጣጠራል፣
- • ከየዲፓርትመንቶቹ የሚቀርቡትን የሕግ ጥናት እና ምርምሮች በአቻላቻ ግምገማ ፣በቴክኒክ ኮሚቴ እንዲገመገሙ ያደርጋል ፣ሂደቱ ይከታተላል፣
- • በስሩ ያሉትን ዲፓርትመንቶች ሥራቸውን ስለሚያስተባብሩበት፣ስለሚያቀናጁበትና ስለሚያቀላጥፉበት መንገድ እያጠና ሃሣብ ያቀርባል፣
- • አግባብ ካለቸው መሥሪያ ቤቶች(ባለድርሻ አካላት) ጋር በመገናኘት በጋራ ሲለሚሰሩ ጥናት እና ምርምሮች እንዲሁም የሥራ ልምድና የመረጃ ልውውጥ ያደርጋል፣

No comments:
Post a Comment