30 Jan 2021

የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ራዕይ፤ ተልዕኮና ዕሴቶች


የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ራዕይ፤ ተልዕኮና ዕሴቶች

የአስተዳደሩ ራዕይ

  • በ1917 ዓ.ም መልካም አስተዳደር የሰፈነበት የህግ እና የታራሚዎች ሰብአዊ መብት የተከነረበት፤የታረመና የታነጸ ፤ አምራች ህግ አክባሪ ዜጋ የሚፈራበት ተቀም ማድረግ፤
የአስተዳደሩ ተልዕኮ

  • በፍርድ ቤት ዉሳኔ ወይም ትዕዛዝ ማረፊያና ማረሚያ ቤት የሚላኩ የቀጠሮ እስረኞችና ታራሚዎችን በመቀበል የተጠናከረ የጥበቃ ደህንነት እና አስተዳደር ፤ የመሰረታዊ ፍላጎት አቅርቦት ፤ የተሃድሶና ልማት አገልግሎት በመስጠት ታራሚዎችን የወንጀል አስከፊነት ተረድተዉ አምራችና ህግ አክባሪ ዜጋ እንዲሆኑ በማድረግ ተቀሙ ወንጀልን በመከላከል የህዝብን ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ ረገድ የበኩሉን ድርሻ መወጣት፤
እሴቶች
  • የሕግ የበላይነት ማክበር ማስከበር፤
  • ሰባአዊ መብት ማክበር ማስከበር፤
  • ፍትሃዊነት፤
  • ግልጽነትና ተጠያቂነት፤
  • ኪራይ ሰብሳቢነትና ሙስናን መጠየፍ፤
  • በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል፤
  • ማረም ማነጽ ተኮር አገልግሎት፤
  • ለለዉጥ ዝግጁነት፤
  • አርአያነት፤
የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስልጣንና ተግባር

  • በፍ/ቤት ዉሳኔ ወይም ትዕዛዝ መሠረት የሚላኩትን ታራሚዎች በመቀበል ይጠብቃል፤ያርማል፤እንዲሁም ከፍ/ቤት የሚሰጡ ዉሳኔዎችን ያስፈጽማል፤
  • ታራሚዎችን ፍ/ቤት ያቀርባል፤
  • የታራሚዎችን ጤንነት ይጠብቃል፤ነጻ ህክምና ይሰጣል፤ምግብና መጠለያ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ለታራሚዎች አካላዊና ስነልቦናዊ እንከብካቤ አስፈላጊ ተግባሮችን አገልግሎቶችንና እንቅስቃሴዎችን ያካሄዳል፤
  • ታራሚዎች ከተለቀቁ በሓላ እራሳቸዉን ለማስተዳደና ለህግ ተገዠ እንዲሆኑ የሚያችል የቀለም፤የሙያ ስልጠና፤ማህበራዊ እና የምክር አገልግሎት ያሰጣል፤
  • በፍ/ቤት ሲታዘዝ ታራሚዎችን ከፌዴ/ማረ/ቤቶች ወደ ክልል ማረ/ቤቶች አጅቦ ያደርሳል፤
  • ለታራሚዎች በማረ/ቤት ቆይታቸዉ የማረ/ቤቱን የስነ ስርአት መመሪያ በመጣስ ለሚፈጸሙ ጥፋት ደንብና መመሪያ በሚያዘዉ መሰረት የስነ ስርአት ቅጣቶችን የወስናል፤ያስፈጽማል፤
  • በፌደራል ደረጃ ከየማዕከል ማረ/ቤቶች ታራሚዎች በሚመለከት መረጃዎችንና ስታስቲኮችን ያሰባስባል፤የጠናቅራ፤መረጃ ለሚመለከተዉ አካል ይሰጣል፤
  • ታራሚዎች በሚያሳዩት የባህሪ ለዉጥ በሕጉ መሠረት በአመክሮ ወይም በይቅርታ እንዲፈቱ ስልጣን ለተሰጠዉ አካል ሀሳብ ያቀርባል፤
  • አስተዳደሩ ለሥራ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኝ የማረሚያ ጥበቃ አባላትን ይመለምላል፤ይቀጥራል፤ያሰለጥናል፤ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ሲቪል ሠራተኞችን ይቀጥራል፤ያስተዳድራል፤
  • የመ/ቤቱ ሠራተኞች ሙያ ብቃት ለማሣደግ በአገር ዉስጥና በዉጭ አገር የስልጠና እድሎችን ያመቻቻል፤
  • የታራሚዎች አጠባበቅና አያያዝ ለማሻሻል የማረሚያ ጥበቃ አባላትን የሙያ ብቃትና አገልግሎት ደረጃዉን የጠበቀ እንዲሆን የሚረዱ ጥረቶችን ያከናዉናል፤
  • የፌደራል ማረ/ቤቶች አስተዳደር ከክልል ማ/ቤቶች የሙያ፤ የቴክኒክና የምክር አገልግሎት ይሰጣል፤
  • የንብረት ባለቤት ይሆናል፤ዉል ይዋዋላል፤ በራሱ ይከሳል፤ይከሰሳል፤
  • ከስራዉ ባህሪዉ ጋር ተያያዝነት ያላቸዉን ሌሎች ተግባራት ያከናዉናል፤

1 comment:

Popular posts

Recent Posts

LikeBtn

Type

አስተማሪ የሆኑት የችሎት ድራማ ቪዲዮዎች

DOCUMENT & FILES

Criminal Procedure Code 6/2013 PDF by ሕግ እና ፍትህ on Scribd