13 Jun 2020

የስልጣን ክፍፍል የስልጣን ክፍፍል በአገራችን ህገ መንግስታዊ መርህ።

የስልጣን ክፍፍል

የስልጣን
ክፍፍል በአገራችን ህገ መንግስታዊ መርህ ሲሆን ህግ አውጭው፤ ህግ ተርጓሚውና ህግ አስፈፃሚው ያላቸውን ስልጣን ከፋፍሎ ያስቀምጣል፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ መርህ በተቃራኒ የአስተዳደር ህግ ከተግባራዊ ምክንያቶች የተነሳ ስራ አስፈፃሚው አካል ሕግ ከማስፈፀም ስልጣኑ በተጨማሪ ህግ የማውጣትና ህግ የመተርጐም ተግባራትን እንዲያከናውን በልዩ ሁኔታ ይፈቅዳል፡፡ እነዚህ ተደራራቢ ስልጣናት የመንግስት አስተዳደርን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ በልዩ ሁኔታ የተሰጡ እንጂ በመርህ ደረጃ ከስልጣን ክፍፍል መሰረተ ሀሳብ ጋር ይጋጫሉ፡፡ ስለሆነም የህገ መንግስቱ የስልጣን ክፍፍል መርህ የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ደንብና መመሪያ የማውጣት እና ዳኝነታዊ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን በአፈፃፀም ረገድ በጠባቡ እንዲተረጐም በማድረግ የዚህ ስልጣናቸው ገደብ ሆኖ ያገለግላል፡፡
ይኸው መርህ ፍርድ ቤቶች ሚናቸው እስከየት ድረስ እንደሚዘልቅ ይወስናል፡፡ መደበኛ ፍ/ቤት በህግ ተለይተው በታወቁ የምርመራ ምክንያቶች ስልጣን ካልተሰጠው በስተቀር በስልጣን ውስጥ የተፈፀመ ድርጊት ከማረም መቆጠብ ይኖርበታል፡፡ ፍ/ቤቶች በስልጣን ውስጥ የተፈፀመ ድርጊትን የሚያርሙ ከሆነ በስራ አስፈፃሚው ስልጣን ጣልቃ በመግባት የስልጣን ክፍፍል መርህን ይጥሳሉ፡፡
የስልጣን ክፍፍል
የስልጣን ክፍፍል በአገራችን ህገ መንግስታዊ መርህ ሲሆን ህግ አውጭው፤ ህግ ተርጓሚውና ህግ አስፈፃሚው ያላቸውን ስልጣን ከፋፍሎ ያስቀምጣል፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ መርህ በተቃራኒ የአስተዳደር ህግ ከተግባራዊ ምክንያቶች የተነሳ ስራ አስፈፃሚው አካል ሕግ ከማስፈፀም ስልጣኑ በተጨማሪ ህግ የማውጣትና ህግ የመተርጐም ተግባራትን እንዲያከናውን በልዩ ሁኔታ ይፈቅዳል፡፡ እነዚህ ተደራራቢ ስልጣናት የመንግስት አስተዳደርን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ በልዩ ሁኔታ የተሰጡ እንጂ በመርህ ደረጃ ከስልጣን ክፍፍል መሰረተ ሀሳብ ጋር ይጋጫሉ፡፡ ስለሆነም የህገ መንግስቱ የስልጣን ክፍፍል መርህ የአስተዳደር መስሪያ ቤቶች ደንብና መመሪያ የማውጣት እና ዳኝነታዊ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን በአፈፃፀም ረገድ በጠባቡ እንዲተረጐም በማድረግ የዚህ ስልጣናቸው ገደብ ሆኖ ያገለግላል፡፡
ይኸው መርህ ፍርድ ቤቶች ሚናቸው እስከየት ድረስ እንደሚዘልቅ ይወስናል፡፡ መደበኛ ፍ/ቤት በህግ ተለይተው በታወቁ የምርመራ ምክንያቶች ስልጣን ካልተሰጠው በስተቀር በስልጣን ውስጥ የተፈፀመ ድርጊት ከማረም መቆጠብ ይኖርበታል፡፡ ፍ/ቤቶች በስልጣን ውስጥ የተፈፀመ ድርጊትን የሚያርሙ ከሆነ በስራ አስፈፃሚው ስልጣን ጣልቃ በመግባት የስልጣን ክፍፍል መርህን ይጥሳሉ፡፡


ስለ ህግ ትርጉም

ስለ ህግ ትርጉም።


የህግ ትርጉም አስፈላጊ የሚሆነው አወዛጋቢ ክርክሮች (cases and controversies) ሲኖሩ፣ ወይም አንድን ነገር ማድረግ (action) ወይም አለማድረግ (omission) ከህጎች ተቃርኗል ተብሎ ሲገመት ነው።

ግልፅ የሆኑ የሕገ-መንግስት አንቀፆች ያለተጨማሪ ማብራሪያና ትርጉም በቀጥታ የሚፈፀሙ ድንጋጌዎች (self-executing provisions) በመሆናቸው በአብዛኛው ትርጉም አያስፈልጋቸውም። ለትርጉም ተጋላጭ የህግ ድንጋጌዎች ቅድመ ሁኔታን የሚያስቀምጡ: “በግልፅ ካልተደነገገ በስተቀር” (unless provided by law)፣ ወይም “ዝርዝር ጉዳዮ በሌላ ህግ ይወሰናል” (particulars shall be determined by law) የመሳሰሉ ዐረፍተ-ነገሮችን ያዘለ ሊሆን ይችላል። ሕግን የመተርጎም ዋናው አላማ የህጉን መንፈስ ለመረዳትና ለማብራራት እንጂ ክፍተት ተጠቅሞ አዲስ ህግ ለመፍጠር መሆን የለበትም።
      የፌደሬሽን ምክር ቤት የተረጎማቸው አብዛኞቹ የህገ-መንግስት ጉዳዮች ከመደበኛ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ ተሰጥቶባቸው ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት የተመሩ ሲሆን፣ አሁን አስፈፃሚው ያቀረበው ህገ-መንግስት ትርጉም ጥያቄ ግን ከዚህ በፊት ፍርድ ቤት አይቶት ስለማያውቅና ጉዳዩ የሚታየው በተሻሻለው አዋጅ 789/2005 መሰረት አንቀፅ 5 “ከፍርድ ቤት ውጭ ስለሚቀርብ የትርጉም ጥያቄ” ስር ስለሆነ፣ በሌላ መልኩ፣ የቀረበውን የሕገ-መንግስት ጥያቄ በተመለከተ መሰረት የጣሉ ተመሳሳይ የፍርድ ቤትም ይሁን የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔዎች (precedents) ካለመኖር አኳያ፣ በአለም ተቀባይነት ያላቸውን የህገ-መንግስት አተረጓጎም መርሆዎች (principles of interpretation)፣ እና ያንዳንድ ሃገራት የፍርድ ውሳኔዎችን ከኢትዮጵያ ስርዐተ-ህግ፣ የመንግስት አወቃቀር፣ ፖሊቲካዊና ማህበራዊ መስተጋብር አኳያ መቃኘት ተገቢ ነው።



ከላይ የተገለፀውን ሃሳብ ለማጠናክር የፌደሬሽን ምክር ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ 789/2005 እንደሚጠቁመው: “ምክር ቤቱ የሚቀርቡለትን ሕገ-መንግስ ጉዳዮች መርምሮ ለመወሰን ጠቃሚ ናቸው ብሎ የሚያምንባቸውን የህገመንግስት አተረጓጐም መርሆዎች መለየትና በስራ ላይ” በማዋል፣…ለምክር ቤቱ የቀረበው ጥያቄ በሕገ-መንግስቱ የሰፈሩትን መሰረታዊ መብቶች እና ነፃነቶች የሚመለከት ሲሆን ትርጉሙ ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውን አለማቀፍ ሰብአዊ ህግጋት ከአለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ህግ ጋት፣ አለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ስምምነቶችና የአለማቀፍ ሰነዶች መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መንገድ” እንደሚተረጎም አቅጣጫ ይሰጣል።

(1) በኢትዮጵያ፣ “የቅድመ ምርጫ ዝግቶች እና ምርጫ በሚደረግበት ወቅት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የሚያስገድድ ሁኔታ ቢከሰት፣ በዚህም የተነሳ ምርጫ ማድረግ የማይቻል ቢሆን የምርጫ ዘመናቸው ያበቃው ምክር ቤቶች እና የአስፈፃሚው አካል የስራ ዘመን ምን ይሆናል?”

አስፈፃሚው ካነሳው የሕገ-መንግስት ትርጉም ጥያቄ በተገናኘ ሊነሱ የሚችሉ አንዳንድ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት ድንጋጌዎች ከተለያዩ የአተረጓጐም ስልቶች አኳያ:



(ሀ) ቀጥተኛ ወይም ሌጣ ትርጉም/Textualism/: መጀመሪያ ህጉን ያወጡት ሰዎች ቃል በቃል፣ በቀጥታ “ምን ቃል ነበር የተጠቀሙት?” ብሎ በመጠየቅ የህጉን ሌጣ ትርጉም (plain meaning) መመልከትና በቀጥታ ጥቅም ላይ ማዋል (direct application) ነው።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 58 (1): “የምክር ቤቱ የሥራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እስከ ሰኔ ሰላሳ [በመሆኑ]..”

ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕ/መ አንቀጽ 60 (1): “ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን ዘመኑ ከማለቁ በፊት… ምክር ቤ[ቱን መበተን ስላለበት…]፣

ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕ/መ አንቀጽ 60 (3): ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን ዘመኑ ከማለቁ በፊት ምክር ቤቱን ከበተነ “ከስድስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አዲስ ምርጫ መደረግ” ስለሚጠበቅበት” (የበተነው አዲስ ምርጫ ለማድረግ ከሆነ)፤ በሌላ መልኩ፣ ከላይ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕ/መ አንቀጽ 58 (1) የምክር ቤቱ አምስት አመት የሥራ ዘመን በግልፅ ስለተወሰነና በአንቀጽ 58 (3) የፓርላማው አምስት አመት እድሜ ሰኞ፣ ሰኔ ሰላሳ መሆኑ በግልፅ በመገደቡና ከዛ በላይ ሊራዘም ስለሚችልበት ድንጋጌ በየትኛውም የህገ-መንግስቱ ክፍል ስላልተገለፀ፣

ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕ/መ አንቀጽ 54 (1): “የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት… በየአምስት ዓመቱ በሕዝብ” ስለሚመረጡ፤ በሌላ መልኩ፣ በ አንቀጽ 60 (3): ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን ዘመኑ ከማለቁ በፊት ምክር ቤቱን በአንቀጽ 58 (1) እንደተገለፀው የመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ሰኔ ሰላሳ ከመድረሱ በፊት መበተን ስላለበት፣

በአንቀጽ 58 (3) መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚመረጠው ለአምስት ዓመታት [ስለሆነና]፤ የሥራ ዘመኑ ከማብቃቱ ከአንድ ወር በፊት አዲስ ምርጫ [ተካሂዶ ስለሚጠናቅርቅ]፤ በመጨረሻም፣

በ ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕ/መ አንቀጽ 106 መሰረት የ ሕገ-መንግሥቱ “የአማርኛ ቅጂ የመጨረሻው ሕጋዊ እውቅና ያለው ሰነድ” ስለሆነ በአማርኛ ቛንቛ ደግሞ፣ “ሰኞ፣ ሰኔ ሰላሳ” በ ሰኔ 29 እና ሃምሌ 1 መካከል የሚገኝ ቀን ከመሆን ውጭ ሌላ ተለዋጭ ትርጉም ስለሌለው፣ በቀጥተኛ አተረጓጎም (textually)፣ ሰኞ፣ ሰኔ ሰላሳ የምክር ቤቱና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የስራ ዘመን ያበቃል ማለት ነው።

(ለ) የህጉ የመጀመሪያው ቅጂ ትርጉም/Original Meaning/: አንዳንድ የህገ-መንግስት ሊቃውንት የመጀመሪያ ቅጂ/የኦሪጂናላዊ (originalist/nontexological) ያተረጓጐም መርህን ከቀጥተኛ አተረጓጐም መንገድ (textualism) ጋር ሲያቀላቅሉት ቢታይም ነገር ግን  ሁለቱ የተለያዩ ናቸው። ኦሪጂናላዊ ትርጓሜ ህጉን ቃል በቃል በመተርጎም ብቻ የሚወሰን ሳይሆን፣ ህጉ በፀደቀ ዚጌ የነበሩት ሰዎች ሊረዱት ከሚችለው እይታ (perspective) እና አገባብ (context) በመነሳት የህጉን መንፈስ ለመረዳት መሞከር ነው።

የዛሬ 25 አመት የተፃፈው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሕገመንግስት ረቂቅ (draft) 105 አንቀፆች ነበሩት:: አሁን በስራ ላይ ያለው፣ የፀደቀው ደግሞ 106 አንቀፆች አሉት:: ከአስፈፃሚና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስራ ዘመን ጋር በተያያዘ በሁለቱ ሰነዶች መካከል መሰረታዊ የፍሬ ነገር (substantive) ልዩነት የለም።

ለምሳሌ፣ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስራ ዘመን ጋር በተያያዘ የሁለቱን ቅጂዎች አንቀፆች እናነፃፅር:

● በስራ ላይ ያለው የ ኢ.ፌዴ.ሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 58 (3): “የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚመረጠው ለአምስት ዓመታት ነው፤ የሥራ ዘመኑ ከማብቃቱ ከአንድ ወር በፊት አዲስ ምርጫ ተካሂዶ ይጠናቀቃል” ሲል፣

● ረቂቁ የ ኢ.ፌዴ.ሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 58 (3) ደግሞ : “…የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስራ ዘመኑ ከማብቃቱ ከአንድ ወር በፊት አዲስ ምርጫ መደረግ አለበት::” ይላል።

የመጀመሪያው ጠበቅ ያለ (conservative) ቢመስልም፣ የሁለቱም ሰነዶች መንፈስ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስራ ዘመኑ ከማለቁ አንድ ወር ቀደም ብሎ ብሄራዊ ምርጫ በማካሄድ ቀጣዩን ምክር ቤት መተካት እንዳለበት አፅንኦት ለመስጠት ነው።

● የ ኢ.ፌዴ.ሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 72 (3) ክፍተት ይኖረው ይሆን?

ህግ አውጪው በወቅቱ ያልታዘባቸው ወይም ያልገመታቸው ሁኔታዎች ዛሬ ላይ ጥያቄ ሲያስነ

ሱ፣ ተቀባይነት ያላቸውን መርሆዎች በመከተል ሕጉን መተርጎም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።

አንቀጽ 72 (3): “በዚህ ሕገ-መንግሥት መሰረት በሌላ አኳሗን ካልተወሰነ በስተቀር የጠቅላይሚኒስትሩ የሥራ ዘመን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን ነው” የሚለውን ገልብጠን ስናነበው፣ በሌላ አኳሓን ከተገለፀ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የስራ ዘመን ምክር ቤቱ ከተበተነም በሗላ ሊቀጥል ይችል ይሆናል ለማለት ይሆን? የአርቃቂዎቹ ሃሳብ (legislators’ intent) ጥያቄ ውስጥ የሚገባው እንግዲህ እዚህ ላይ ነው::

ህጉን ባረቀቁት ሰዎች ሃሳብ (intent)፣ “የጠቅላይ ሚኒስትሩን የስልጣን ዘመን ከምክር ቤቱ የስልጣን ዘመን ትንሽ ረዘም ማድረግ የሚቻልበትን ሁኔታ ለመክፈት አስበው ወይም ሕገ-መንግስታዊ ቅርቃር (gridlock) ሲከሰት የአስፈፃሚው የስራ ዘመን እንደ አስፈላጊነቱ ከመደበኛው የስራ ዘመን ትንሽ ረዘም እንዲል አስበው ይሆን?” ብለን ለመጠየቅ፣ በመጀመሪያ፣ በሌላ አኳሗን የ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን ስለሚራዘምበት አጋጣሚ የሚገልፅ (በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ) ድንጋጌ መኖር አለበት።

ለምሳሌ፣ በማይናማር (Maynamar) ሕገ- መንግስት፣ የኢትዮጵያ አይነት ሁኔታ ሲከሰት፣ አስፈፃሚው ከተፈቀደለት የስራ ዘመን ለተጨማሪ ጊዜ መቆየት እንደሚችል ይገልፃል። ድንጋጌው ስላለ፣ ክርክር ቢነሳ ተርጓሚው አካል ጉዳዩን ሊመለከተው ይችላል። Maynamar Constitution, Article 61 (a).

በኢትዮጵያ ህግ ግን ከዚህ ጋር የሚቀራረብ ድንጋጌ የለም፣ የሕጉ አርቃቂዎች ሃሳብም ይህን በሚመለከት የሚጠቁመው ፍንጭ ወይም ለትርጉም ተጋላጭ ድንጋጌ የለም። ባጭሩ፣ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተጠቅሞ ህዝባዊ ምርጫን ማራዘም ስለሚቻልበት ሁኔታና አጋጣሚ የሚገልፅ የህገ-መንግስቱ ድንጋጌ የሕጉ አርቃቂዎች ሃሳብም የለም።

● አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የምርጫ ሰሌዳ:

“የሕዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ…” እንደሚያውጅ ተመልክቷል። በዚህ አዋጅ፣ ለህዝብ ጥቅም ሲባል፣ ዴሞክራሲያዊ መቶችም ሳይቀሩ ሊገደቡ የሚችልበት አጋጣሚ እንዳለ ይገልፃል። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዴሞክራሲያዊ መብቶች ላይ ገደብ መጣል ማለት ግን፣ በህገመንግስቱ የተወሰነውን የምርጫ ቀን እስከማስቀየር ይደርሳል ማለት አይደለም። የኢ.ፌዴ.ሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 93 ከ 72 እና 58 በጣምራ ሲነበቡ፣ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሂደት ላይ እያለ የስራ ዘመኑ የሚያልቅበት አስፈፃሚ፣ በቀጣይ ሊተካው ለሚችለዉ አዲስ አስፈፃሚ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አስተላልፎ ከማለፍ ውጭ፣ በሕገ-መንግስቱ ከተፈቀደለት የስራ ዘመኑ ተሻግሮ በሃገሪቱ መፃኤ የፖለቲካና ማህበራዊ ሁኔታዎች ዛሬ ላይ ከስራ ዘመኑ ባሻጋር መወሰን የሕገ-መንግስቱን የበላይነት የሚፃረር ብቻ ሳይሆን፣ የመንግስት የስልጣን ክፍፍል መርሆን (principle of separation of power) በመቃረን ሌሎቹን የመንግስት አካላት የሚገዳደር ይሆናል:: የአስፈፃሚ የማስፈፀም ስልጣን ከስልጣን ዘመን ማብቃት ጋር አብሮ ያከትማል (የ ኢ.ፌዴ.ሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 72 [3])

(ሐ) መሠረት የጣሉ የፍርድ ውሳኔዎች (Stare Decisis or Judicial Precedents): የኢትዮጵያ የፍትህ ስርአት በይበልጥ በተፃፉ ህጎች (codified laws) መሰረት በመሆኑና፣ ይህን አወዛጋቢ የህግ ክርክር በሚመለከት ከዚህ በፊት ለትርጉም ቀርቦ የሚያውቅ ጉዳይ ወይም ተቀራራቢ ውሳኔ ባለመኖሩ፣ በሌላ መልኩ የፌደሬሽን ምክር ቤት ከዚህ በፊት ትርጉም የሰጠባቸው ክርክሮችም ቢሆኑ ለጉዳዩ በቀጥታ መልስ የሚሰጡ ስላልሆኑ፣ የዚህ አይነት የአተረጓጎም ዘዬ ለጊዜው ብዙም አስፈላጊ ላይሆን ይችላል።

(መ) አወንታዊ ምልከታ /Pragmatism/: የዚህ አተረጓጎም ዋና ትኩረት፣ የሚተረጎመዉ ጉዳይ (ቢተረጎም) የሀገሪቱ ቋሚ ህግ ስለሚሆን፣ ውሳኔው ከሌሎች ህጎች ጋር የሚኖረውን ተቃርኖ በማጤን፣ የህዝብ አቋም መመሪያ (public policy) አንፃር በሀገሪቱ፣ በህዝቧና የፖሊቲካ ስርአቱ ላይ የሚያደርሰውን አሉታዊ ጫናን ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ህገ-መንግስት ከህግነቱ በተጨማሪ የፖለቲካ ሰነድም ስለሆነ፣ “ለፖለቲካዊ ችግሮች ፖለቲካዊ መፍትሄ” ከሚል እሳቤ በመነሳት ህጉን ከነባራዊ ሁኔታ በማጣጣም ለመተርጎም መሞከር ነው። ችግሩ፣ አስፈፃሚው ይሄን ያተረጓጎም ዘዬ በመጠቀም በ “ፐብሊክ ፖሊሲ እና የህዝብ ጥቅም” ሰበብ አይነኬ (nonderogatory) የህገመንግስት ድንጋጌዎችን ሳይቀር ለመሸራረፍና የግል የፖለቲካ አጀንዳዎችን ለመሰንቀር እድል መክፈቱ ነው።

አሁን ካለው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ፣ አስፈፃሚው “ለህዝብ ጤና” በሚል የምርጫ ሰሌዳን የመቀየር እርምጃው፣ ያንን ተከትሎ ያቀረበው “የሕገ-መንግስት ይተርጎምልኝ” ጥያቄ ወደዚህ ያተረጓጎም ስልት ያደላ የትርጉም ፍላጎት እንዳለው ይጠቁማል። የ አስፈፃሚው አካል የምርጫ ማራዘም ውሳኔና ያንን ተከትሎ የሚፈጠረው የስልጣን ክፍተት (power vacuum) ለበጎ ነው ብለው ውሳኔውን የሚደግፉት እንዳሉ ሁሉ፣ ከፍተኛ ተቃውሞ እና ሃገራዊ ውዝግብ በማስከተሉ፣ ብሎም በቀጣይ የምርጫ ሂደት ተአማኒነት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዳያሳድር፣ የ አገር አለመረጋጋትና የዴሞክራሲ ተቋማት መናጋትን ግምት ውስጥ ያስገባ ገንቢ የትርጉም አቀራረብ መከተል ጠቃሚ ነው (መተርጎም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኝ)። መሠረታዊ የህገ-መንግስት ጥያቄ በይበልጥ ከህግ አንፃር በመመልከት፣ በቀጣይ ጠንካራ ሕብረብሄራዊ ሕገ-መንግስታዊነትን (multinational constitutionalim) ለማጠናከር ይረዳል።

(ሠ) የመንግስት አወቃቀርና ግንኙነት/Structuralism/: በመሰረቱ፣ የዚህ አይነቱ የህገ-መንግስት አተረጓጎም የህገ-መንግስቱን ስሪት፣ በፌደራል እና የክልል መንግስታት መካከል (ፌሰራሊዝም) እና በሶስቱ የመንግስት አካላት መካከል ያለውን ግንኙነት (የስልጣን ክፍፍል)፣ ብሎም በመንግስትና በዜጎች መካከል የሚኖረውን መስተጋብር ግምት ውስጥ ያስገባ አተረጓጎም ስልት ነው። የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ስርዐት በክልልሎችና የፌደራል መንግስቱ በጥምር ሉአላዊነት (dual sovereignty) የሚገለፅ በመሆኑ፣ የፌደራል አስፈፃሚው አካል ርምጃዎችና ውሳኔዎች የክልሎችን ሉአላዊነት ከተጋፋ የህገ-መንግስቱ መሰረታዊ መርሆዎች ተጣሱ ማለት ነው።

(ረ) ታሪካዊ ልምዶች /Historical Practices/: ኢትዮጵያ፣ ሕገ-መንግስቱ ከመፅደቁ ጥቂት አመታት ቀደም ብሎ ለመበታተን ጫፍ ላይ ደርሳ የነበረች ሃገር መሆኗ ሲታሰብ፣ የሕጉ አርቃቂዎች ሃሳብ (legislative intent) ሕብረብሄራዊ ሕገ-መንግስታዊነትን መመስረት እንደነበር መገመት አያዳግትም። በመሆኑም፣ ይህ የአተረጓጎም መርሆ ከላይ የተጠቀሱትን የጋራ እሴቶችን ከማስጠበቅ አኳያ ነው ሕገ-መንግስታዊነትን የሚመዝነው።  የኢትዮጵያ ያለፈ ታሪክ በተጨባጭ የሚያሳየው፣ ሕገ-መንግስት መብቶችን ለማስጠበቅ የተቀረፀ ሰነድ በመሆኑ፣ ከሕዝቦች ሉአላዊት በሚቃረን መልኩ የሚወሰዱ ማናቸውም የፌደራል አስፈፃሚ ውሳኔዎች ህገመንግስታዊ መሰረት አይኖራቸው።

ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አኋያ የህገ-መንግስት ተርጓሚ አካል የላይኛው ምክር ቤት ወይም የፌደሬሽን ምክር ቤት ቢሆንም፣ ምንም እንኳ የአሜሪካ የፍትህ ስርዐት፣ የፌደራሊዝም ስሪት እና ተጨባጭ ሁኔታዎች ከኢትዮጵያ ቢለይም፣ የ ሕገ-መን

ግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤው የአሜሪካን ህገ-መንግስት ሳይንስ ፍልስፍና (constitutional jurisprudence) ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ በማጣጣም የህገ-መንግስት ክለሳ ስራ ቢተገብር ጠቃሚ ጎኖች አሉት። በ ኢትዮጵያ የፍትህ ስርዐት የፍርድ ክለሳ (judicial review) የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ስልጣን ሕገ-መንግስታዊ መሰረት ቢኖረውም፣ ህገ-መንግስቱን የመተርጎም የወል ስልጣን ግን የለውም::

የፍርድ ውሳኔዎችን ህገ-መንግስታዊነት የመከለስ ደረጃዎች (Standards of Judicial Review) በኢትዮጵያ:
የፌደሬሽን ምክር ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ 789/2005 አንቀፅ 7 (1): “ለአጣሪ ጉባኤው የሚቀርብ የሕገመንግስት ትርጉም ጥያቄ አቀራረብ በአዋጁ በሚወጣ መመሪያ መሰረት ይሆናል” ይላል። የህገ-መንግስት ማጣራት ሂደቱ የሚከተላቸውን የህገመንግስት መርሆዎችን (standards of review) ቢገልፅ መልካም ነው።

የአሜሪካ የፍርድ መከለስ ሂደት (judicial review process) ህጎች ወይም ድርጊቶች ከሕገ-መንግስቱ መቃረናቸውን ለመገምገም በሶስት የተለያዩ መሰረታዊ ደረጃዎች ይመረምራል:

● “Rational Basis” (ምክንያታዊ/ቀላል)- ለምሳሌ፥ የግለሰብ ተንቀሳቅሶ የመስራት መብትን የሚገድብ ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌ ጥያቄ ዉቅስጥ ሲገባ፤

● “Intermediate Basis” (መካከለኛ)- ፍርድ ቤቶች ሕገመንግስታዊነቱን የሚመረምሩት ህግ ወሳኝ የመንግስት ጥቅምን የሚያራምድ መሆኑን በማየት መመርመር ፤

● “Strict Scrutiny” (በጥልቀት መፈተሽ መመርመር)-ለምሳሌ: የአንድን ቡድን፣ ብሄር፣ ዘር፣ ወይም ግለሰብ  መሰረታዊ መብትን ለመገደብ አስፈፃሚው አካል በፍርድ ክርክር ወቅት የማስረዳት ሸክሙ (burden of proof) እጅግ ከፍ ያለ ነው፣ ምክንያቱም የግለሠብም ሆነ የቡድን ነፃነትን ለመገደብ መንግስት እጅግ አሳማኝ ምክኒያት ሊኖረው ስለሚገባ:: በሌላ መልኩ መንግስት የዜጎችን ነፃነትና ሉአላዊነት አደጋ ውስጥ እንዳይከት ከለላ ለመስጠት፣ የህጎችናን ድርጊቶችን ህጋዊነት የሚመረምረው ፍርድ ቤት በአስፈፃሚው አካል የሚወሰድ እርምጃን ህገመንግስታዊነትን ጠበቅ ባለ መስፈርት ይገመግማል።

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኢትዮጵያ፣ የምርጫ መራዘም፣ የክልሎች ሉአላዊነትና ሕብረብሄራዊ ፌደራሊዝም:

የስልጣን ምንጭ ሕዝብ በመሆኑና ለህዝብ ቅርበት ያላቸው ደግሞ የአካባቢ መስተዳድሮች (local governments) ስለሆኑ፣ ከፌደራል መንግስት ይልቅ ክልሎች በይበልጥ የሉአላዊነት መገለጫ ናቸው። የክልሎች ስብስብ የፌደራል መንግስት ስለሚፈጥር፣ የፌደራል መንግስት የክልሎች ፖለቲካዊ ፍጥረት ነው ማለት ይቻላል። የክልሎችን ሕገ-መንግስታዊ ሉአላዊነት በሚጋፋና፣ የጥምር ሉዐላዊነትን መርሆን ግምት ውስጥ ሳያስገባ የምርጫ ማራዘም ውሳኔ የፌደራል አስፈፃሚው መወሰኑ መሰረታዊ የሉአላዊነት መርሆን ስለሚፃረር፣ ጉባኤው የትርጉም ጥያቄውን የሚመረምረው ከላይ በአሜሪካ ስርዐት (strict  scrutiny) በመሰለ ጥብቅ ምርመራ መሆን አለበት፣ በሌላ መልኩ ጥያቄውን ያቀረበው አስፈፃሚ ከፍ ያለ የማስረዳት ሸክም (burden of proof) አለበት።

ለምሳሌ፣ የትግራይ ክልላዊ መንግስት፣ የፌደራሉን ሕገ-መንግስት ተንተርሶ ባፀደቀው ህገመንግስት፣ የክልሉን ህዝብ የሉአላዊ ስልጣን ባከቤትነት ለማረጋገጥ ብሎም የመንግስት አስተዳደርን ለማስቀጠል፣ የነዋሪዎቹን ጤና አደጋ በማይጥል መልኩ “ምርጫ ለማድረግ ወስኛለሁ” ይላል። በሌላ መልኩ፣ የፌደራሉ አስፈፃሚ ከዚህ የተለዬ አቛም አለው። የ ፌደራሉ አስፈፃሚ አካል የምርጫ ማራዘም ውሳኔ በፌደራሉንም ሆነ የክልል ሕገ-መንግስታት፣ ኢትዮጵያ ፈርማ የሕጓ አካል ያደረገቻቸውን አለማቀፍ ስምምነቶች በመጣስ፣ የክልሎችን ሉዐላዊነት በመጋፋቱ የሕገመንግስቱን  መሰረታዊ መርሆዎች ይፃረራል።

የመምረጥና መመረጥ መብት ወሳኝ ዴሞክራሲያዊ መብት መሆኑ ግልፅ ነው። በኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀጽ 38 (1) መሰረት “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቀለም፣ በዘር፣ በብሔር፣…ልዩነት ሳይደረግበት… በመረጣቸው ተወካዮች አማካኝነት በሕዝብ ጉዳይ አስተዳደር የመሳተፍ መብት” እንዳለው ይገልፃል። በትግራይ ክልል ህገ- መንግስት መሰረት ደግሞ፣ የክልሉ ህዝብ በክልሉ ጉዳይ ላይ የሉአላዊነት ባለቤት እንደሆነ፣ በአንቀፅ 8 ( 9) ሉአላዊነቱ የሚገለፀው ደግሞ የክልሉ ነዋሪዎች በቀጥተኛ ዴሞክራሲያዊ ሂደት በመረጧቸው ተወካዮቻቸው እንደሆነ፣ ይህ መብት በምንም መልኩ ሊገደብ እንደማይችል አንቀፅ 9 (1) ያስረግጣል።

በተመሳሳይ፣ በአማራ ክልል ህገ-መንግስት ምእራፍ ሁለት፣ አንቀፅ 8 ንኡስ አንቀፅ 2 መሰረት፣ የክልሉ ህዝብ የሉአላዊ ስልጣን ባለቤት እንደሆነና፣ ይህ ሉአላዊነት የሚገለፀው ደግሞ፣ በሚመርጧቸው ተወካዮች እና ራሳቸው በቀጥታ በሚያደርጉት ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ እንደሆነ ይገልፃል።

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ጨምሮ ማናቸውም የአስፈፃሚ አካል ፖሊቲካዊ እርምጃዎች “ለዜጎች ጥቅም” በሚል የዜጎችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን (በተለይም የመምረጥና መመረጥ መብትን) ሊገድብ እንደማይገባ፣ የኢትዮጵያ ህገ- መንግስት ምንጭ፣ በሗላም አካል በሆነው፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአለማቀፍ ሰብአብዊና ፖለቲካዊ መብቶች ቃልኪዳን (ICCPR: Part One, Article 1) ላይ በግልፅ ተቀምጧል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለዜጎች ደህንነትና ጤና ሲባል መፈፀሙ አስፈላጊነቱ ባያከራክርም፣ ራሱ ሕገ-መንግስቱ ከለላ የሰጣቸውን መሰረታዊ በራስ ጉዳይ የመወሰን መብቶች፣ የክልሎችን ሉዐላዊነት በመጋፋት፣ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶችን አደጋ ላይ በሚጥል መልኩ የሚወሰድ የአስፈፃሚ ርምጃ ኢ-ህገመንግስታዊ ይሆናል። ግልፅ የጥቁር ቀለም የሕገ-መንግስት ድንጋጌዎች ሲጣሱ የህገመንግስት ትርጓሜ የሚያስፈልግበት አገባብ የለም።

ጉዳዩ ያገባኛል ስለማለት (Locus Standi) እና የአንድ ወገን አቤቱታ (One-sided Petition):

ህገ መንግስቱን የሚቃረን ውሳኔ ሲከሰት የትርጉም ጥያቄውን ለምክር ቤት ማቅረብ ያለበት በውሳኔው ያልተስማማ ሌላ ሶስተኛ ወገን ነው ወይስ ከ ህገ-መንግስቱ የሚቃረን ውሳኔ ወስኛለሁ ብሎ የሚያምነዉ ራሱ አስፈፃሚው አካል (በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኩል አሰፀድቆ ማቅረብ ሌላ ጉዳይ ነው)?

የሕገ-መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤው መሰረት በሆነው የ ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕ/መ 84 (2) መሰረት: “በፌዴራሉ መንግሥትም ሆነ በክልል ሕግ አውጪ አካላት የሚወጡ ሕጐች ከዚህ ሕገ መንግሥት ጋር ይቃረናሉ የሚል ጥያቄ ሲነሳና ጉዳዩም በሚመለከተው ፍርድ ቤት ወይም በባለ ጉዳዩ ሲቀርብለት መርምሮ ለመጨረሻ ውሳኔ ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ያቀርባል” በማለት የጉባኤውን ተግባርና አላማ ያብራራል።

የሕገ-መንግስቱን ድንጋጌ አንቀፅ 84ን ለማሟላት በወጣው በተሻሻለው አዋጅ 789/2005 መሰረት: “በማንኛውም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን የመጨረሻ ውሳኔ … መብቴና ነፃነቴ ተጥሷል የሚል ማንኛውም ሰው… ለ ጉባኤው…ማቅረብ ይችላል” ይላል። በ በርካታ ሃገራት ህጎች “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም አርቲፊሻል ሰው ሊሆን ይችላል። አስፈፃሚውን እንደ ተቋም (juridical person) እንውሰድና፣ ራሱ የምርጫ ማራዘም ሃሳብ ለምርጫ ቦርድ አቅርቦ፣ የራሱ ውሳኔ ከህግ ጋር ስለተጋጨበት እንዲተረጎምለት ጥያቄ የሚያቀበው ራሱ አስፈፃሚው ይሆናል ማለት ነው። እንግዲህ፣ የሕገ-መንግሥ

ት ትርጉም ጥያቄ የሚያቀርበው ያንድ ወገን አቤቱታ አቅራቢ (lone petitioner) ሌላ ወገን ተቃራኒ ሃሳብ ማቅረብ በማይችልበት ሁኔታ፣ የአጣሪ ጉኤው፣ ከዛም አለፍ ብሎ ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት ጉዳዩ ከቀረበ፣ ምክር ቤቱ፣ የሁለት ወገን ሃሳብ እንዳያይ የ “ይተርጎምልኝ” ጥያቄው አቀራረብ ጉዳዩን አስቸጋሪ ያደርገዋል።

አስፈፃሚው “የራሴ ውሳኔ ከገ ሕገ-መንግስቱ ጋር ተቃርኖብኛል” ብሎ የፌደሬሽን ምክር ቤትን “ተርጉምልኝ” ማለቱ፣ ከመጀመሪያውኑ የምርጫ ማራዘም ውሳኔው ሕገ-መንግስታዊ መሰረት ስለሌለው አከራካሪ እንደሆነና፣ ዞሮ ዞሮ ጉዳዩ ፌደሬሽን ምክር ቤት ለትርጉም ሊሄድ እንደሚችል አስፈፃሚው ተስፋ በማድረግ ቀድሞ እያወቀ የወሰደው እርምጃ ነበር ማለት ነው። ያለበለዚያ፣ “ጉዳዩ የህግ ትርጉም ያስፈገዋል” ወይም “ሕገ-መንግስቱን ተቃርኗል” የሚለው ጥያቄ ይመጣ የነበረው፣ በአስፈፃሚው የምርጫ ማራዘም ውሳኔ ቅር በተሰኝ ሌላ ሶስተኛ ወገን ይሆን ነበር። አጣሪ ጉባኤው፣ “አስፈፃሚው የሕገመንግስት ትርጉም ጥያቄ ለማቅረብ የሚገባው ወገን (real party in interest) መሆኑንም መጠየቅ ይኖርበታል።

(2) “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲታወጅ ምክንያት የሆነው ክስተት ከተወገደ በሗላ [ምርጫውስ] በምን ያክል ጊዜ ውስጥ ሊከናወን ይገባል?”

ሁተኛው ፍሬነገር ከህግ ትምህርት ቤት የመላምት ጉዳይ (hypothetical case) ጋር ይመሳሰላል። ገና የመጀመሪያው፣ ዋናው ጉዳይ እልባት ሳያገኝ (አስፈፃሚው መቼ፣ ምን እንደሚያደርግ ሳይታወቅ)፣ በፖለቲካ ውሳኔ ባንዣበበበት ሁኔታ) የህግ አስተያየት መሰንዘር ብዙም ጠቃሚ ባይሆንም፣ በሕገ-መንግስቱ ድንጋጌ አንቀጽ 54 (1) ምርጫ በየአምስት አመቱ መደረግ ስላለበት እንዲሁም 58 (3): “የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚመረጠው ለአምስት ዓመታት…፤ የሥራ ዘመኑ ከማብቃቱ ከአንድ ወር በፊት አዲስ ምርጫ ተካሂዶ ስለሚጠናቀቅና አስፈፃሚው እንደሚለው ምርጫውን ማድረግ ስላልተቻለ፣ የኮሮናቫይረስ በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ስርጪት መጠን ተገምግሞ፣ ከአስፈላጊ ጥንቃቄ ጋር በተቻለ ፍጥነት ምርጫ ቢደረግ፣ ዜጎች በፈቀዱትን መንግስት የመተዳደር ሕገ-መንግስታዊ መብታቸውን በተቻለ ፍጥነት እንዲጎናፀፉ ያግዛል።

ማጠቃለያ፥
ሕገ-መንግስት የህግና የፖለቲካ ስነድ ከመሆኑ አኳያ የፖለቲካ ውሳኔዎችም ችግር ፈቺ ሊሆኑ ቢችሉም፣ ግልፅ የሆኑ፣ ራሳቸው በራሳቸው የሚፈፀሙ (self-executing) የጥቁር ቀለም ሕጎችን መተርጎም ግን አዲስ ህግ ለመፍጠር ከመሞከር አይለይም።

አማራጭ አንድ: ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኮሮናቫይረስ ስርጪት ተገምግሞ፣ ከከፍተኛ ጥንቃቄ ጋር በተቻለ ፍጥነት ምርጫ በማድረግ ቅቡል የመንግስት አስተዳደር ማስቀጠል፤

አማራጭ ሁለት: በአግባቡ በተጠና በቂ መረጃ መሰረት የቫይረሱ ስርጭት ምርጫ ለማድረግ እንደማያስችል ሃገራቀፍ መግባባት ከተደረሰና ሰኔ ካለፈ፣ ህብረብሄራዊ፣ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያሳተፈ የአደራ መንግስት (caretaker government) በማቛቛም፣ የአደራ አስተዳደሩ ምርጫ በማካሄድ ስልጣን ለሚመረጥ ፓርቲ ወይም የፖርቲዎች ጥምረት ማስተላለፍ፤

አማራጭ ሶስት:
ሁለተኛው ካልተቻለ፣ የሃገሪቱ ርእሰ ብሄር (ፕሬዝደትን) ብሄራዊ ምርጫ ተካሂዶ ሌላ መንግስት እስኪተካ ሃገሪቱን በአደራ መንግስትነት ቢያስተዳድሩ (የርእሰ ብሄር የስራ ዘመን ከጠቅላይ ሚኒስቴር በአንድ አመት በመብለጡ የሚፈጠረውን የስልጣን ክፍተት (power vacuum) በመሸፈን የሽግግር ሂደቱን ሊመሩ ይችላሉ

12 Jun 2020

አስገድዶ መድፈር› የሚለው ቃል የተገኘው ‹ራፒዮ› ከሚለው ቃል ነው ፣ ፍችውም ‹መያዙ› ማለት ነው

_**አስገድዶ መድፈር› የሚለው ቃል የተገኘው ‹ራፒዮ› ከሚለው ቃል ነው ፣ ፍችውም ‹መያዙ› ማለት ነው ፡፡*_

ስለሆነም አስገድዶ ማስገደድ በኃይል ፣ በፍርሀት ወይም በማጭበርበር ያለ ሴቷ ያለ አስገድዶ የመያዝ ወይም የሴቶች ጥፋት ነው ፡፡

ከሴት ጋር ስምምነት መደረግን በማስገደድ ማስገደድን ያካትታል ፡፡ አስገድዶ መድፈር የሴት የግል ሰው እንደ አንድ የጥቃት ድርጊት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ፣ ይህም በማንኛውም መንገድ አስጸያፊ ነው። የሴት ራስ መጎዳት የመጨረሻው ጥሰት ነው ፡፡  የሕንድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት “ሞት የማያስከትለው ውርደት እና በሰው ልጆች ክብር ላይ የተጣለው አስከፊ ወንጀል” በማለት በትክክል ገልጾታል ፡፡  አስገድዶ መድፈር አካላዊ ጥቃት ብቻ አይደለም ፣ ነገር ግን የተጠቂውን ሰው አጠቃላይ ገጽታ ሁሉ ያጠፋል።

የጋብቻ አስገድዶ መድፈር አንድ ሰው ከሚስቱ ጋር በኃይል ፣ በኃይል ማስፈራራት ፣ ወይም በአካል ብጥብጥ ወይም ፈቃድ መስጠት በማይችልበት ጊዜ አላስፈላጊ የግብረ-ሥጋ ግንኙነትን ያሳያል ፡፡  የጋብቻ አስገድዶ መድፈር ምናልባት በኃይል ብቻ በመጠቀም ፣ በመደብደብ አስገድዶ መድፈር ወይም አሳዛኝ / አስከፊ የሆነ አስገድዶ መድፈር ሊሆን ይችላል ፡፡  ባል በአካል አካላዊም ሆነ ወሲባዊ በሆነባት ሚስት ላይ ባልተለመደ ሁኔታ የጥፋተኝነት እርምጃ ነው…

11 Jun 2020

የህግ የበላይነት


የህግ የበላይነት
ብዙ ምሁራን በየፊናቸው በምርምርና ጥናት ባገኙት እውቀት ተመርኩዘው የህግ የበላይነት መርህ ምንነት፤ ይዘትና ፋይዳውን አስመልክቶ አያሌ ንድፈ ሀሳባዊ ትንታኔዎችን አቅርበዋል፡፡ በአገራችን ደግሞ አባቶችና እናቶች በልባቸው ከተጻፈው እውነትና ከልምድ ከቀዱት ቱባ እውቀት በመነሳት የህግ የበላይነትን ጽንስ ሀሳብ በአንድ አባባል እንዲህ ይገልጹታል፡፡
“በፍርድ ከሄደች በቅሎዬ ያለፍርድ የሄደች ዶሮዬ!”
የዚህ ተረትና ምሳሌ አንኳር መልዕክት ለጥቂት ሰዎች ብቻ የተገለጠ ሳይሆን በመላው ማህበረሰብ ዘልቆ የገባ ሀቅ ነው፡፡ እናም ይህን የህግ የበላይነት ፅንሰ ሓሳብን ጠንቅቆ ያወቀው ማህበረሰብ ህግ ሲጣስ፤ ፍትህ ሲጓደል፤ መብት ሲታፈን፤ ስርዓት አልበኝነት ሲነግስ፤ ማን አለብኝነትና በዘፈቀደኝነት ሲንሰራፋ፤ የግሉ የሆነችው ዶሮ ከህግ እና ከፍርድ ውጭ ሲቀማ ድምፁን አጉልቶ ይጮሀል፤ በህግ አምላክ! ይላል፡፡ የጮኸው የዶሮዋ ዋጋ አንገብግቦት አይደለም፡፡ የተወሰደችበት መንገድ እንጂ፡፡ በፍርድ ከሆነ፤ በህጉ መሰረት ከሆነ እንኳንስ ለዶሮ ለበቅሎም ቄብ አይሰጠውም፡፡
በህዝብ አስተዳደር፤ ፖለቲካ ሳይንስ፤ ህግ እና በሌሎችም የጥናት መስኮች የሚገኙ ምሁራን ስለ የህግ የበላይነት ምንነትና ይዘት ያላቸው ግንዛቤና አስተሳሰብ የተራራቀ ከመሆኑ የተነሳ ጽንሰ ሀሳቡ አሁንም ድረስ ቁርጥ ያለ ትርጓሜ አልተገኘለትም፡፡ አንድ የመስኩ ምሁር ይህንን ሀሳብ በማጠናከር እንዳብራራው፤
‘[T]he rule of law’, like ‘democracy’, has no single meaning: it is not a legal rule, but a moral principle, which means different things to different people according to their particular moral positions.a
በዚህ የተነሳ በተለያዩ አገራት የፖለቲካና የህገ መንግስት ስርዓት ውስጥ ይዘቱና አፈጻጸሙ የተለያየ አንዳንዴ የማይጣጣም መልክ በመያዙ መሰረታዊ እሳቤው ወጥነት ርቆታል፡፡
ለምሳሌ በእንግሊዝ አንደኛውና የህግ የበላይነት መገለጫ በመንግስትና በግለሰብ መካከል የሚነሱ ክርክሮች በመደበኛ ፍ/ቤቶች ብቻ መዳኘታቸው ነው፡፡ ያ ማለት በእንግሊዛዊ አይን ፈረንሳይ ውስጥ የህግ የበላይነት የለም እንደ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም በፈረንሳይ በግለሰብና በመንግስት መካከል የሚነሱ ክርክሮች ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ የሚዳኙት ከመደበኛ ፍ/ቤት ትይዩ ራሱን ችሎ በተቋቋመ የአስተዳደር ፍ/ቤት ስርዓት አማካይነት ነው፡፡ በእንግሊዝ ሌላኛው የህግ የበላይነት ትርጉም የግለሰቦች መብትና ነፃነት መደበኛ ፍ/ቤቶች በቀረቡላቸው ተጨባጭ ጉዳዮች የሚሰጡት ውሳኔ ውጤት ነው የሚል ይዘት አለው፡፡ ይህ አስተሳሰብ በእንግሊዝ እውነት ቢሆንም የኛን አገር ጨምሮ የተጻፈ ህገ መንግስት ባላቸው እንደ አሜሪካ ባሉ አገራት የዜጐች መብቶችና ነፃነቶች በህገ መንግስቱ ላይ በጽሑፍ ይዘረዘራል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በሊብራል ዲሞክራሲ ስርዓት ውስጥ የህግ የበላይነት ማለት በህጉ መሰረት ከመግዛትና ከማስተዳደር ባለፈ የህጉ ይዘት (ለምሳሌ ፍትሐዊነቱ፤ የዜጐችን መብት ማክበሩ፣ ህጉ የወጣው ህዝብ ወዶና ፈቅዶ በመረጣቸው ተወካዮች መሆኑ ወዘተ…) ብሎም የገለልተኛና ነፃ ፍ/ቤቶች፤ የዲሞክራዊ ተቋማት፤ ነፃ ፕሬስ ወዘተ… መኖር ሁሉም በህግ የበላይነት ጽንስ ሀሳብ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ የሊብራል ዲሞክራሲ ጠበል አልተጠመቁም በሚባልላቸው መንግስታት (ለምሳሌ በቻይና) ጽንሰ ሀሳቡ ስልጣን ያለው አካል በሚያወጣቸው ህጐች መሰረት መግዛትና ማስተዳደር ላይ ብቻ የተገደበ ነው፡፡
የህግ የበላይነት መርህ የአስተዳደር ህግ (በተለይ በእንግሊዝ) የተተከለበት መሰረት ነው፡፡ በዚህ መርህ መሰረት ስራ አስፈፃሚው፣ የአስተዳደር መ/ቤቶች እና የአስተዳደር ጉባዔዎች የሚሰጡት ውሳኔ በህጉ መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡ በመንግስት አስተዳደር ውስጥ ህጋዊነት የሚሰፍነው ስልጣን የተሰጠው ማናቸውም የመንግስት አካል የሚወስዳቸው እርምጃዎች፣ የሚፈጽማቸው ድርቶች፣ የሚሰጣቸው ውሳኔዎች እና የሚያወጣቸው ደንብና መመሪያዎች በህግ ጥላ ስር መሆናቸው ሲረጋገጥ ነው፡፡
የመንግስት ባለስልጣናት የሚሰጡት ውሳኔ በህግ ከተቀመጠው የስልጣን ክልል በላይ ከሆነ ውሳኔው የህግ የበላይነት መርህን እንደሚጥስ ጥርጥር የለውም፡፡ ህጋዊነት መከበሩን ማረጋገጥ ማለት አስተዳደራዊ ድርጊት፣ ውሳኔ፣ እርምጃ፣ ደንብና መመሪያ በህግ በተቀመጠው የስልጣን ገደብ ውስጥ መሆኑን አሊያም አለመሆኑን ማረጋገጥ ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የመደበኛ የፍርድ ቤቶች ተግባር ነው፡፡ ይህንን ተግባር በሚያሳንስ መልኩ በፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ላይ በህግ አውጭው የሚደረግ ገደብ በውጤቱ የህግ የበላይነት መርህን ይሸረሽራል፡፡ ገደቡ በህግ የበላይነት መርህ ላይ ከሚፈጥረው አደጋ በተጨማሪ የዜጎችን ፍትህ የማግኘት መብት ያጣብባል፡፡ በተለይም ይህ መብት ህገ-መንግስታዊ እውቅና የተሰጠው ከሆነ የፍርድ ቤቶችን ስልጣን መገደብ ዞሮ ዞሮ የዜጎችን ህገ-መንገስታዊ መብት መገደብ ነው፡፡
የህግ የበላይነት መርህ የአስተዳደር ህግ መሰረት ብቻ ሳይሆን ገደብ ጭምር እንደሆነ ማውሳት ያስፈልጋል፡፡ የውሳኔን ህጋዊነት ማረጋገጥ በይዘቱ ላይ መቆጠብን ያስከትላል፡፡ ፍ/ቤቶች የህግ የበላይነት በማስከበር ሚናቸው የአስተዳደራዊ ውሳኔዎች ይዘት እንዳያጣሩ ወይም በፖሊሲ ጥያቄዎች ጣልቃ እንዳይገቡ ይገድባቸዋል፡፡

16 May 2020

11 Feb 2020

መማር ደጉ



መማር ደጉ

ምስክሩ ለችሎቱ የመግቢያ ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጠ ነው፡፡ ስሙን፤ ዕድሜውን፤ መኖሪያ አድራሻውን ከተናገረ በኋላ ዳኛው “የትምህርት ደረጃ?” ሲሉ ጠየቁት

ምሰክር——“አቋርጫለው”
ዳኛ——“ከስንት?”
ምስክር——“ከ1ኛ ክፍል”

1 Oct 2019

የምርጫ ቦርድ

የምርጫ ቦርድ

በፌዴራልና በክልል የምርጫ ክልሎች ነፃና ትክክለኛ ምርጫ በገለልተኝነት እንዲያካሂድ ከማንኛውም ተፅዕኖ ነፃ የሆነ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ይቋቋማል፡፡
የቦርዱ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሾማሉ።
ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡
የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን
የሀገሪቱን የሕዝብ ቁጥር በየጊዜው የሚያጠናና ቆጠራ የሚያካሂድ የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ይኖራል፡፡
የኮሚሽኑ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሾማሉ፡፡
ኮሚሽኑ ዋና ጸሐፊ፣ አስፈላጊ ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ይኖሩታል፡፡

የኮሚሽኑ ዓመታዊ በጀት በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ይጸድቃል፡፡

የሕዝብ ቆጠራ በየአሥር ዓመቱ ይካሔዳል።
በውጤቱም መሠረት የምርጫ ክልሎችን አከላለል የምርጫ ቦርድ በሚያቀርበው ረቂቅ መሠረት የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ይወሰናል፡፡

የኮሚሽኑ ተጠሪነት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው። ስለሥራው አፈጻጸም በየጊዜው ለምክር ቤቱ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ሀሳብን ስለማመንጨት
አንድ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ሀሳብ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምፅ የደገፈው፣ የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምፅ የደገፈው ወይም ከፌዴሬሽኑ አባል ክልሎች ውስጥ አንድ ሦስተኛው የክልል ምክር ቤቶች በድምፅ ብልጫ የደገፉት ከሆነ ለውይይትና ለውሳኔ ለመላው ሕዝብና የሕገ መንግሥቱ መሻሻል ለሚመለከታቸው ክፍሎች ይቀርባል፡፡

ሕገ መንግሥቱን ለማሻሻል

በዚህ ሕገ መንግሥት ምዕራፍ ሦስት የተዘረዘሩት መብቶችና ነፃነቶች በሙሉ፣ ይህ አንቀጽ፤ እንዲሁም አንቀጽ 104 ሊሻሻሉ የሚችሉት በሚከተለው አኳኋን ብቻ ይሆናል፤

ሀ) ሁሉም የክልል ምክር ቤቶች የቀረበውን ማሻሻያ በድምፅ ብልጫ ሲያጸድቁት፣
ለ) የፌዴራሉ መንግሥት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምፅ የቀረበውን ማሻሻያ ሲያጸድቀው፣ እና
ሐ) የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ማሻሻያውን ሲያጸድቀው ነው፡፡

በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ከተዘረዘሩት ውጭ ያሉት

የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች ሊሻሻሉ የሚችሉት በሚከተለው አኳኋን ብቻ ይሆናል፤

ሀ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በጋራ ስብሰባ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ የቀረበውን ማሻሻያ ሲያጸድቁት፣ እና
ለ) ከፌዴሬሽኑ አባል ክልል ምክር ቤቶች ውስጥ የሁለት ሦስተኛ ክልሎች ምክር ቤቶች በድምፅ ብልጫ የቀረበውን ማሻሻያ ሲያጸድቁት ነው፡፡



Popular posts

Recent Posts

LikeBtn

Type

አስተማሪ የሆኑት የችሎት ድራማ ቪዲዮዎች

DOCUMENT & FILES

Criminal Procedure Code 6/2013 PDF by ሕግ እና ፍትህ on Scribd