5 Oct 2020

ከባድ የሰው ግድያ • የአገዳደሉ ሁኔታ አድራጊው በተለይ ጨካኝ፤ ነውረኛ ወይም አደገኛ ሲሆን አንድ ሰው በወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1/ሀ/

       
    ከባድ የሰው ግአኝዋክ ግድያ
የአገዳደሉ ሁኔታ አድራጊው በተለይ ጨካኝ፤ ነውረኛ ወይም አደገኛ ሲሆን

አንድ ሰው በወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1/ሀ/ መሠረት ጥፋተኛ ሆኖ እንዲገኝ በዚሁ አንቀጽ የተጠቀሱት ሁኔታዎች ተሟልተው መገኘት አለባቸው፡፡ እነዚህን ሁኔታዎች ደግሞ ሰውየው ድርጊቱን ለመፈፀም ካነሣሣው ሃሣብ እና ከድርጊቱ አፈፃፀም አንፃር በመመርመር የድንጋጌውን ትክክለኛ አፈጻጸም መለየት ይቻላል፡፡ በድንጋጌው ስለሃሳብ ሁኔታ የሚገልጹትን ሁኔታዎች ስንመለከትም አስቀድሞ የማሰብ ሁኔታ፣ ቂም በቀል፣ ጥላቻ፣ ቅናት ወዘተ… የሚሉ የሚገኙ ሲሆን ከባድ የድርጊት አፈፃፀም መኖርን የሚያመላክቱ ነጥቦች ደግሞ በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 84 ስር የተመለከቱትና በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ በአንቀጽ 86 መሠረት ከባድ ምክንያቶች ናቸው ብሎ የሚቀበላቸውን ሁኔታዎች የሚያካትቱ ናቸው፡፡
አንድ ሰው ከእነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት የሃሣብ ሁኔታዎች ወይም የድርጊት አፈፃፀም አንዱን እንኳ ፈጽሞ ቢገኝ እና ይህም ሁኔታ ሲታይ ገዳዩ “በተለይ” ጨካኝ፤ ነውረኛ ወይም አደገኛ የሚያሰኝ አይነት ሆኖ ከተገኘ በአንቀጽ 539/1/ሀ/ መሠረት ጥፋተኛ ሊሰኝ እና ለዚሁ አድራጎት በሕጉ የተመለከተው የቅጣት ውሳኔ ሊተላለፍበት ይገባል፡፡
አንቀጽ 539/1/ሀ/ በቅድሚያ እንዲሟላ የሚፈልገው መሰረታዊ ነጥብ የአገዳደሉ ሁኔታ አድራጊው በተለይ ጨካኝ፤ ነውረኛ ወይም አደገኛ መሆኑን የሚገልጽ ሆኖ መገኘትን ነው፡፡ በድንጋጌው ስር “በተለይ” የሚለው ቃል የሚያስገነዝበው ከተራ አገዳደል ወይም የሃሣብ ሁኔታ ውጭ በሆነ አድራጐት ወይም ለጥቃት መገልገያ የተደረገው መሣሪያ በሟች ላይ ስቃይና መከራ ማሣደር እንዳለበት፣ ግድያውም ከተራው ሁኔታ የተለየ እንደነበር የሚያመለክት ነው ተብሎ ይታመናል፡፡፡ በህጉ በተለይ ጨካኝ ነውረኛ ወይም አደገኛ መባሉ የአገዳደሉ ሁኔታና የመግደያው መሣሪያ አደገኛነት፣ ፍፁም ጨካኝነትን፤ ነውረኛነትን ወይም የተጋነነ አደገኛነትን ማሳየት እንዳለበት የሚያስገነዝብ ነው፡፡
ስለሆነም የወ.ሕ. አንቀፅ 539(1(ሀ)) የማክበጃ ልዩ ሁኔታዎች በመኖራቸው ምክንያት ሆን ተብሎ የተፈፀመ ግድያ “ከባድ የሰው ግድያ” የሚባልበትን ምክንያቶች የያዘ ነው፡፡ እነዚህ ልዩ ሁኔታዎች በሌሉበት አንድ ተከሣሽ በዚህ አንቀጽ ስር ጥፋተኛ ሊባል የማይችል መሆኑን የሕጉ ይዘትና መንፈስ ያሳያል፡፡ ከእነዚህ እና በተጠቃሹ አንቀፅ በፊደል "ለ" እንዲሁም "ሐ" ስር ከተመለከቱት የድንጋጌዎቹ ማቋቋሚያዎች ውጪ ሆን ተብሎ የሚደረግ ሰው የመግደል ወንጀል የሚያስቀጣው በአንቀጽ 540 ስር ነው፡፡

No comments:

Post a Comment

Popular posts

Recent Posts

LikeBtn

Type

አስተማሪ የሆኑት የችሎት ድራማ ቪዲዮዎች

DOCUMENT & FILES

Criminal Procedure Code 6/2013 PDF by ሕግ እና ፍትህ on Scribd