የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትልቁን የሀገሪቱን የቆዳ ስፋት የያዘ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅትም በ12 አሰተዳደራዊ ዞኖችና በ180 ወረዳዎች የተዋቀረ ነው፡፡ ከነዚህ 12 ዞኖች ውስጥ፣ የባሌና ቦረና ዞኖች 45.7 ከመቶ የሚሆነውን የክልሉን መሬት ሲይዙ በህዝብ ሰፈራ ረገድ ግን የክልሉን 14 ከመቶ ብቻ ይኖርባቸዋል፡፡ የኦሮሚያ ምክር ቤት የክልሉ አስተዳደር ከፍተኛው መዋቅር ነው፡
በክልሉ የከተማ አካባቢዎች ግን 67.8 ከመቶ የኦርቶዶክስ ክርስትያን፣ 24.0 ከመቶ የእስልምና እንዲሁም 7 ከመቶ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነው፡፡ በብሄር ስብጥር አኳያም 85 ከመቶ የኦሮሞ፣ 9.1 ከመቶ የአማራ፣ 1.3 ከመቶ የጉራጌ፣ የተቀረው 4.6 ከመቶ የሌሎች ብሄረሰቦች ይኖራሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በላቲን ፊደላት የተቀረፀው የኦሮሚኛ ቋንቋ የክልሉ የስራ ቋንቋ ሲሆን 85.5 ከመቶ በክልሉ ይነገራል፣ አማርኛ 11 ከመቶ፣ ጉራጊኛ 0.98 ከመቶ፣ ጌዴኦኛ 0.98 ከመቶ እንዲሁም ትግርኛ 0.25 ከመቶ በክልሉ የሚነገሩ ቋንቋዎች ናቸው፡፡
ዋነኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትከሚገኘው ህዝብ 90 ከመቶየሚሆነው ህዝብ ኑሮውን የግብርና ስራ ላይ ያደረገ ነው፡፡ በክልሉ በቆሎ፣ ገብስ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ሽንብራ እና ባቄላ እንዲሁም የተለያዩ የቅባት እህሎች በከፍተኛ ደረጃ የሚመረቱ ሰብሎች ናቸው፡፡ ቡና ለገበያ የሚቀርብ ምርት ነው፡፡ ክልሉ 51.2 ከመቶ የሚሆነውን የሰብል ምርት ከዚህም ውስጥ 45.1 ከመቶ የሚሆነው ጊዜያዊ ሰብሎች፣ እንዲሁም 44 ከመቶ የሚሆነውን የቁም ከብት ሀብት ለሀገሪቱ ያበረክታል፡፡የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፍትህ አካላት ፡-

እናመሰግናለን
ReplyDeleteእድሜ ይስጥህ
ReplyDelete