20 Oct 2020

ችሎት ቀልዶች

 3 ልጆች አላት፡፡ ልክ ነው?
መልስ - አዎ
ጥያቄ - ከእነዚህ ውስጥ ወንዶች አሉ?
መልስ - የሉም
ጥያቄ - ሴቶችስ?
¶¶
ጥያቄ - ዛሬ ጠዋት በችሎት መሀላ ስትሰጥ እዛው ፍርድ ቤት ውስጥ ነበርክ?
¶¶
ጥያቄ- ስለዚህ እስክትመለስ ድረስ ሄደህ ነበር ማለት ነው?
¶¶
ጥያቄ - በዚህ ከተማ ውስጥ ህይወትህን በሙሉ ኖረሃል?
መልስ - አይ ገና ነኝ፡፡
¶¶
ጥያቄ - የአቶ ሃንቲንግተንን ሬሳ የመረመርክበትን ሰዓት በግምት ታውቀዋለህ?
መልስ - የሬሳ ምርመራው በ12፡30 ላይ ተጀመረ፡፡ ወደ ማታ አካባቢ ነበር
ጥያቄ - በዛን ሰዓት አቶ ሃንቲንግተን ሞቶ ነበር?
መልሰ - ኧረ በጭራሽ! የኔ ደንቆሮ! ለምን የሬሳ ምርመራ እንደማደርግለት ተገርሞ እያየኝ ነበር
¶¶
ጥያቄ - ዕቃው ምን እንደሆነ ወይም ምን እንደሚመስል አላውቅም ብለሃል፡፡ ግን ግን ቢያንስ ልትገልጸው ትችላለህ?
¶¶
ጥያቄ - የ20 ዓመቱ፤ ትንሹ፤ የመጨረሻው ልጅ ዕድሜው ስንት ነበር?
¶¶
ጥያቄ- መኪናዎቹ በተጋጩበት ወቅት ምን ያልህ ተራርቀው ነበር?
¶¶
ጥያቄ - አቶ ስሌተር የተንደላቀቀ የጫጉላ ሽርሽር ላይ ነበርክ፡፡ ልክ ነኝ?
መልስ - አዎ ልክ ነው፡፡ በአውሮፓ አገራት ተዘዋውሬአለሁ፡፡
ጥያቄ - ለመሆኑ አዲሷን ሚስትህን ይዘሃት ነበር የምትዞረው?
¶¶
ጥያቄ - የሽንት ናሙና ለመስጠጥ ብቁ ነህ?
መልስ - እንዴታ! ለዛውም ከልጅነቴ ጀምሮ ነዋ!
¶¶
ጥያቄ - ከሟች ጋር ትተዋወቃላችሁ?
መልስ - አዎ እንተዋወቃለን
ጥያቄ - ከመሞቱ በፊት ወይም በኋላ?
¶¶
ጥያቄ - ስምህ ማነው?
መልስ - ኤርነስት ማክዶዌል
ጥያቄ - የጋብቻ ሁኔታ?
መልስ - ደህና ነው፡፡ ምንም አይልም፡፡
¶¶
ጥያቄ - ውሻውን በጆሮዎቹ ይዞ ወደላይ አንስቶታል?
መልስ - አላነሳውም
ጥያቄ - እሺ የውሻውን ጆሮዎች ምን ሲያደርጋቸው ነበር?
መልስ - አየር ላይ ወደላይ እያነሳቸው
ጥያቄ - በዛን ጊዜ ውሻው የት ነበር?
መልስ - ጆሮዎቹ ላይ ተጣብቆ
¶¶
ጥያቄ - ከተከሳሽ ጋር ያለህ ዝምድና ምንድነው?
መልስ - የወለድኳት ልጄ ነች
ጥያቄ - በፌብሩዋሪ 13 ቀን 1979 ዓ.ም. ላይም ልጅህ ነበረች?
¶¶
ጥያቄ - ከዛ በኋላ ምን ሆነ?
መልስ - ወደ ቤት መጣ፡፡ የሚቀጥለው ቀን ጠዋት ሞቶ ተገኘ
ጥያቄ - ያ ማለት የሚቀጥለው ቀን ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ ሞቶ ነበር ማለት ነው?
¶¶
ጥያቄ - አንተ ከቆምክበት ቦታ ላይ ሆነህ እሱ ይታህ ነበር?
መልስ - አዎ ጭንቅላቱ ይታኝ ነበር
ጥያቄ - ጭንቅላቱ የት ነበር?
መልስ - ከትከሻው በላይ
¶¶
ጥያቄ - እስፐርም መኖሩ ምንድነው የሚያሳየው?
መልስ - ግብረስጋ ግንኙነት እንደነበረ ያሳያል
ጥያቄ - የወንድ እስፐርም ወይስ…?
መልስ - እኔ የማውቀው የወንድ ብቻ ነው
¶¶
ጥያቄ - ባልሽ ያን ቀን ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ መጀመሪያ ከአፉ የወጣው ቃል ምን ነበር?
መልስ - “ካቲ የት ነኝ?” ብሎ ጠየቀኝ
ጥያቄ - እና ለምንድነው ይሄ አንቺን ያስጨነቀሽ?
መልስ - የኔ ስም ሱዛን ነው፡፡
¶¶
ጥያቄ - የልደት ቀንህ መቼ ነው?
መልስ - ጁላይ 15
ጥያቄ - የትኛው ዓመት?
መልስ - እያንዳንዱ ዓመት
¶¶
ጥያቄ - ይህ መድኃኒት የማስታወስ ችሎታህን ቀንሶታል?
መልስ - አዎ
ጥያቄ - እንዴት እንደቀነሰው እስቲ ንገረን?
መልስ - ብዙ ነገር እረሳለሁ
ጥያቄ - ትረሳለህ? እስቲ ከረሳሃቸው ነገሮች መካከል አንዱን ንገረን?
¶¶
ጥያቄ - ከአንቺ ጋር የሚኖረው ልጅሽ ዕድሜው ስንት ነው?
መልስ - 35 ወይም 38 በትክክል አላስታውስም
ጥያቄ - ከአንቺ ጋር ለምን ያህ ጊዜ ኖሯል?
መልስ - አርባ አምስት ዓመት
¶¶
ጥያቄ - በስራ ላይ መጠጥ ትጠጣለህ?
መልስ - ኧረ በፍፁም! ጠጥቼ ወደስራ ካልመጣሁ በስተቀር ስራ ላይ ሆኜ አልጠጣም
¶¶
አንድ የቴክሳስ ጠበቃ “ደደብ!” ሊያስብለው የሚችል ጥያቄ ሊናገር መሆኑ በቅጽበት ሲረዳው እንዲህ ብሎ ነበር፡፡
“ክቡር ፍርድ ቤት! የሚቀጥለው ጥያቄዬን መዋጥ እፈልጋለሁ፡፡”

No comments:

Post a Comment

Popular posts

Recent Posts

LikeBtn

Type

አስተማሪ የሆኑት የችሎት ድራማ ቪዲዮዎች

DOCUMENT & FILES

Criminal Procedure Code 6/2013 PDF by ሕግ እና ፍትህ on Scribd